Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 46:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ ያዕቆብ ያዕቆብ ብሎ ለእስራኤል ተናገረው። እርሱም፦ እነሆኝ አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔርም ሌሊት በራእይ ለእስራኤል ተገልጦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ጠራው። እርሱም፣ “እነሆ፤ አለሁ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እግዚአብሔርም በሌሊት ራእይ፦ “ያዕቆብ ያዕቆብ” ብሎ ለእስራኤል ጠራው። እርሱም፦ “እነሆኝ” አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር፥ ሌሊት በራእይ ተገለጠለትና “ያዕቆብ! ያዕቆብ!” ብሎ ጠራው። እርሱም “አቤት ጌታ ሆይ፥ እነሆ አለሁ” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሌ​ሊት ራእይ፥ “ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ” ብሎ ለእ​ስ​ራ​ኤል ተና​ገ​ረው። እር​ሱም “ምን​ድን ነው?” አለ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 46:2
23 交叉引用  

ከዚህ ነገር በኍላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል፤ አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።


አብራምንም አለው፤ ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንዲሆኑ በእርግጥ እወቅ ባሪያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።


እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ እንዲህም አለው፤ እነሆ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ምውት ነህ እርስዋ ባለ ባል ናትና።


ከእነዚም ነገሮች በኋላ እግዚአብሔር አብረሃምን ፈተነው፥ እንዲህም አለው፦ አብረሃም ሆይ። አብረሃምም፦ እንሆ፥ አለሁ አለ።


የእግዚአብሔር መልአክም ከሰማይ ጠራና፦ አብርሃም አብርሃም አለው፤


የእግዚአብሔርም መልአክ በሕልም፦ ያዕቆብ ሆይ አለኝ እኔም፦ እነሆኝ አልሁት።


እግዚአብሔርንም መፍራት ባስተማረ በዘካርያስ ዘመን እግዚአብሔርን ይፈልግ ዘንድ ልብ አደረገ፤ እግዚአብሔርንም በፈለገ ጊዜ እግዚአብሔር ነገሩን አከናወነለት።


በሌሊት ሕልም አሳብ ሲነሣ፥ የከበደም እንቅልፍ በሰው ላይ ሲወድቅ፥


የዚያን ጊዜም ምሥጢሩ በሌሊት ራእይ ለዳንኤል ተገለጠለት፥ ዳንኤልም የሰማይን አምላክ አመሰገነ።


እነሆም፥ አንድ ሰው በመጋላ ፈረስ ተቀምጦ በሌሊት አየሁ፥ እርሱም በሸለቆው ውስጥ ባሉ በባርሰነት ዛፎች መካከል ቆሞ ነበር፥ በስተ ኋላውም መጋላና ሐመር አንባላይም ፈረሶች ነበሩ።


እርሱም፦ ቃሌን ስሙ፤ በመካከላችሁ ነቢይ ቢኖር፥ እኔ እግዚአብሔር በራእይ እገለጥለታለሁ፥ ወይም በሕልም እናገረዋለሁ።


የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል፦


ጴጥሮስ ሆይ፥ ተነሣና አርደህ ብላ የሚልም ድምፅ ወደ እርሱ መጣ።


ከቀኑም ዘጠኝ ሰዓት ያህል፦ “ቆርኔሌዎስ ሆይ” የሚለው የእግዚአብሔር መልአክ ወደ እርሱ ሲገባ በራእይ በግልጥ አየው።


ራእይም ለጳውሎስ በሌሊት ታየው፤ አንድ የመቄዶንያ ሰው፦ “ወደ መቄዶንያ ተሻገርና እርዳን” እያለ ቆሞ ሲለምነው ነበር።


በደማስቆም ሐናንያ የሚሉት አንድ ደቀ መዝሙር ነበረ፥ ጌታም በራእይ፦ “ሐናንያ ሆይ፥” አለው። እርሱም፦ “ጌታ ሆይ፥ እነሆኝ” አለ።


በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ፦ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ።


እግዚአብሔርም ጌዴዎንን፦ ከአንተ ጋር ያለው ሕዝብ በዝቶአል፥ ስለዚህ እስራኤል፦ እጄ አዳነኝ ብሎ እንዳይታበይብኝ እኔ ምድያምን በእጃቸው አሳልፌ አልሰጣቸውም።


በዚያም ሌሊት እግዚአብሔር፦ በእጅህ አሳልፌ ሰጥቻቸዋለሁና ተነሥተህ ወደ ሰፈር ውረድ።


እግዚአብሔርም መጥቶ ቆመ፥ እንደ ቀድሞውም፦ ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም፦ ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለ።


እግዚአብሔር ሳሙኤልን ጠራው፥ እርሱም፦ እነሆኝ አለ።


跟着我们:

广告


广告