Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 45:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ዮሴፍም ለወንድሞቹ፦ እኔ ዮሴፍ ነኝ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ ነውን? አለ። ወንድሞቹም ይመጠው ነበርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ዮሴፍም ወንድሞቹን፣ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ ለመሆኑ አባቴ እስካሁን በሕይወት አለ?” ሲል ጠየቃቸው። ወንድሞቹ ግን በፊቱ ተደናግጠው ስለ ነበር መልስ ሊሰጡት አልቻሉም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ዮሴፍም ለወንድሞቹ “እኔ ዮሴፍ ነኝ፥ አባቴ እስከ አሁን በሕይወቱ አለን?” አለ። ወንድሞቹም፥ በፊቱ ደንግጠው ነበርና፥ ሊመልሱለት አልቻሉም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ዮሴፍ ወንድሞቹን “እኔ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕይወት አለን?” አላቸው። ወንድሞቹ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ መልስ መስጠትም ተሳናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ዮሴ​ፍም ለወ​ን​ድ​ሞቹ፥ “እኔ ወን​ድ​ማ​ችሁ ዮሴፍ ነኝ፤ አባቴ እስከ አሁን በሕ​ይ​ወቱ ነውን?” አላ​ቸው። ወን​ድ​ሞ​ቹም ይመ​ል​ሱ​ለት ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ ደን​ግ​ጠው ነበ​ርና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 45:3
14 交叉引用  

አሁንም ኑ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፦ ክፋ አውሬም በላው እንላለን ከሕልሞቹም የሚሆነውን እናያለን።


እንዲህም አደረጉ። እነርሱ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፦ በእውነት ወንድማችንን በድለናል እኛን በማማጠን ነፍሱ ስትጨነቅ አይተን አልሰማነውምና ስለዚህ ይህ መከራ መጣብን።


ሮቤልም መልሶ እንዲህ አላቸው፦ ብላቴናውን አትበድሉ ብያችሁ አልነበረምን? እኔም አልሰማችሁኝ፥ ስለዚህ እነሆ አሁን ደሙ ይፈላለገናል።


እርሱም ደኅንነታቸውን ጠየቃቸው እንዲህም አለ፦ የነገራችሁኝ ሽማግሌ አባታችሁ ደኅና ነውን? ገና በሕይወት አለን?


ስለዚህ በፊቱ ደነገጥሁ፥ ባሰብሁም ጊዜ ከእርሱ ፈራሁ።


አሁን ግን በአንተ ላይ መጥቶአል፥ አንተም ደከምህ፥ ደርሶብሃል፥ አንተም ተቸገርህ።


በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፥ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፥ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


ሁሉ አይተውታልና፥ ታወኩም። ወዲያውም ተናገራቸውና፦ አይዞአችሁ፤ እኔ ነኝ፥ አትፍሩ አላቸው።


ስምዖን ጴጥሮስ ግን ባየ ጊዜ በኢየሱስ ጕልበት ላይ ወድቆ፦ ጌታ ሆይ፥ እኔ ኃጢአተኛ ነኝና ከኔ ተለይ አለው።


በሁለተኛውም ዮሴፍ ለወንድሞቹ ታወቀ፥ የዮሴፍም ትውልድ በፈርዖን ዘንድ ተገለጠ።


ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው።


እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።


跟着我们:

广告


广告