Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 45:26 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እንዲህም ብለው ነገሩት፦ ዮሴፍ ገና በሕይወት ነው እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል። ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ አላመናቸውም ነበርና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 አባታቸውንም፣ “እነሆ ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በግብጽ ምድር ሁሉ ገዥ ሆኗል” ብለው ነገሩት። ያዕቆብም በድንጋጤ ክው አለ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እዚያም እንደ ደረሱ አባታቸውን “ዮሴፍ በሕይወት አለ፤ እንዲያውም በመላው ግብጽ ላይ አስተዳዳሪ ሆኖአል” አሉት። ያዕቆብ ግን እጅግ ደነገጠ፤ ሊያምናቸውም አልቻለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እን​ዲ​ህም ብለው ነገ​ሩት፥ “ልጅህ ዮሴፍ በሕ​ይ​ወቱ ነው፤ እር​ሱም በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖ​አል።” ያዕ​ቆ​ብም ልቡ ደነ​ገጠ፤ አላ​መ​ና​ቸ​ው​ምም፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 45:26
17 交叉引用  

የዮሴፍንም ቀሚስ ወሰዱ የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነከሩት።


ወንዶች ልጆቹም ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት ተነሠ መጽናናትን እንቢ አለ እንዲህም አለ፦ ወደ ልጄ ወደ ሙታን ስፍራ እያዘንሁ እወርዳለሁ። አባቱም ስለ እርሱ አለቀሰ።


ወደ አባታቸውም ወደ ያዕቆብ ወደ ከነዓን ምድር መጡ የደረሰባቸውንም ነገር ሁሉ እንዲህ ብለው አወሩ፦


አባታቸውን ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፦ ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ ዮሴፍ የለም ስምዖንም የለም ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ፤


እርሱም አለ፦ ልጅሴ ከእናንተ ጋር አይወርድም ወንድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀርቶአልና በምትሄዱበት መንገድ ምናልባት ክፋ ነገር ቢያገኘው ሽምግልናዬን በኅዘን ወደ መቃብር ታወርዱታላችሁ።


አንዱም ከእኔ ወጣ፦ አውሬ በላው አላችሁኝ እስከ ዛሬም አላየሁትም፤


እነርሱም ሄዱ ከግብፅ አገርም ወጡ ወደ ከነዓንም ምድር ከአባታቸው ከያዕቆብም ዘንድ ደረሱ።


እስራኤልም ዮሴፍን፦ ፊትህን አያለሁ ብዬ አላሰብሁም ነበር እነሆም እግዚአብሔር ዘርህን ደግሞ አሳየኝ አለው።


እነርሱ ባልታመኑ ጊዜ ሳቅሁላቸው፥ የፊቴንም ብርሃን አላወረዱም።


ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን እንደ ሰማ አላምንም ነበር።


ይህም ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም።


እነርሱም ከደስታ የተነሣ ገና ስላላመኑ ሲደነቁ ሳሉ፦ በዚህ አንዳች የሚበላ አላችሁን? አላቸው።


跟着我们:

广告


广告