ዘፍጥረት 45:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ዮሴፍም በእርሱ ዘንድ ቆመው ባሉት ሰዎች ሁሉ ፊት ሊታገሥ አልተቻለውም፦ ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ ብሎ ጮኽ ተናገረ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በዚያ ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩ ሰዎች ፊት ስሜቱን ሊገታ ባለመቻሉ፣ “እዚህ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፤ ስለዚህም ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ጊዜ፣ ከርሱ ጋራ ሌላ ማንም ሰው አልነበረም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ዮሴፍም በእርሱ ዘንድ ቆመው ባሉት ሰዎች ሁሉ ፊት ሊታገሥ አልተቻለውም፦ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፥ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ ማንም ከአጠገቡ የቆመ አልነበረም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ዮሴፍ የናፍቆት ስሜቱን በአገልጋዮቹ ፊት መቈጣጠር ባለመቻሉ “ሁላችሁም ከዚህ ውጡ” ብሎ አዘዘ፤ ስለዚህ ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ በገለጠ ጊዜ ማንም የውጪ ሰው በአጠገቡ አልነበረም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ዮሴፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታገሥ አልተቻለውም፥ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ተናገረ፤ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም። 参见章节 |