Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 44:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ እንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ እኔ ባርያን በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖንን ያህል የተከበርህ ስለ ሆንህ፣ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ይሁዳም ወደ ዮሴፍ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታዬ ሆይ፤ እኔ አገልጋይህ አንዲት ቃል ብቻ ልናገር፤ አንተም የፈርዖን ያህል የተከበርህ ስለሆንህ፥ እባክህን እኔን አገልጋይህን አትቈጣኝ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ይሁዳ ወደ ዮሴፍ ቀርቦ እንዲህ አለ፤ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ አንድ ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ፤ ምንም እንኳ የፈርዖንን ያኽል የተከበርክ ብትሆን እባክህ አትቈጣኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ይሁ​ዳም ወደ እርሱ ቀረበ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ በፊ​ትህ አን​ዲት ቃልን እን​ድ​ና​ገር እለ​ም​ና​ለሁ፤ እኔን አገ​ል​ጋ​ይ​ህን አት​ቈ​ጣኝ፤ አንተ ከፈ​ር​ዖን ቀጥ​ለህ ነህና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 44:18
19 交叉引用  

እርሱም ጌታዬ አይቆጣ እኔም እናገራለሁ ምናልባት ከዚያ ሠላሳ ባገኝ አላጠፋም አለ።


እርሱም፥ እኔ ደግሞ አንድ ጊዜ ብቻ ብናገር ጌታዬ አይቆጣ፤ ምናልባት ከዚያ አሥር አላጠፋትም አለ።


እርሱ አላቸው፦ እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፤


እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና እነሆም የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።


ወንድሞቹም፦ በእኛ ላይ ልትነግሥብን ይሆን? ወይስ ልትገዛ ይሆን? አሉት። እንደ ገናም ስለ ሕልሙና ስለ ነገሩ ይልቁን ጠሉት።


አንተ በቤቴ ላይ ተሾምክ ሕዝቤም ሁሉ ለቃልህ ይታዘዝ እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ።


ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ እኔ ፈርዖን ነኝ በግብፅ አገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁንም እግሩንም አያንሣ።


እርሱም እላቸው፦ ይህን አደርግ ዘንድ አይሆንልኝም ጽዋው የተገኘበቱ ሰው እርሱ ባሪያ ይሁነኝ እናንተም ወደ አባታችሁ በደኅና ውጡ።


ሴቲቱም፦ እኔ ባሪያህ ለጌታዬ ለንጉሥ አንድ ቃል ልናገር አለች፥ እርሱም፦ ተናገሪ አለ።


ነገር ግን ንግሥቲቱ አስጢን በጃንደረቦቹ እጅ በላከው በንጉሡ ትእዛዝ ትመጣ ዘንድ እንቢ አለች፥ ንጉሡም እጅግ ተቈጣ፥ በቍጣውም ተናደደ።


ኢዮብ ሆይ፥ አድምጥ፥ እኔንም ስማ፥ ዝም በል፥ እኔም እናገራለሁ።


አሮንም እንዲህ አለ፦ ጌታዬ ሆይ፥ ቁጣህ አይቃጠል፤ ይህ ሕዝብ ክፋትን እንዲወድድ አንተ ታውቃለህ።


አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፥ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፥ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ ተናገራቸው።


ስለ ሰጠው ታላቅነት ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ሁሉ በፊቱ ይንቀጠቀጡና ይፈሩ ነበር፥ የፈቀደውን ይገድል፥ የፈቀደውንም በሕይወት ያኖር ነበር፥ የፈቀደውንም ያነሣ፥ የፈቀደውንም ያዋርድ ነበር።


ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ፥ ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም። ወልድን የማያከብር የላከውን አብን አያከብርም።


ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው።


跟着我们:

广告


广告