Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 43:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እስራኤልም አባታቸው እንዲህ አላቸው፦ ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህንን አድርጉ ከተመሰገነው ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ ጥቂት በለሳን ጥቂት ማር ሽቱ፥ ከርቤ፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፣ ጥቂት ማር፣ ሽቱ፣ ከርቤ፣ ተምርና አልሙን በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከዚህ በኋላ አባታቸው እስራኤል እንዲህ አላቸው፤ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ፤ ምድሪቱ ከምታፈራው ምርጥ ነገሮች ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ከርቤ ተምርና ለውዝ በየስልቻችሁ ይዛችሁ ለዚያ ሰው እጅ መንሻ ውሰዱለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ መሄዳችሁ የማይቀር ከሆነ ለአገረ ገዢው ገጸ በረከት የሚሆን ምድራችን ከምታፈራው ምርጥ ነገር ሁሉ በስልቻዎቻችሁ ጨምራችሁ ሂዱ፤ ይኸውም በለሳን፥ ማር፥ ቅመማ ቅመም፥ ከርቤ፥ ተምርና ለውዝ ይዛችሁ ሂዱ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አባ​ታ​ቸው እስ​ራ​ኤ​ልም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ነገሩ እን​ዲህ ከሆ​ነስ ይህን አድ​ርጉ ፤ ከም​ድሩ ፍሬ በዓ​ይ​በ​ታ​ችሁ ይዛ​ችሁ ሂዱ፤ ለዚ​ያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለ​ሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 43:11
37 交叉引用  

ያዕቆብም አለ፦ እንደዚህ አይደለም ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።


እንጀራም ሊበሉ ተቀመጡ ዓይናቸውንም አንሥተው አዩ፥ እነሆም የእስማኤላውያን ነገዶች ወደ ግብፅ ለመውረድ ከገለዓድ መጡ ግመሎቻቸውም ሽቱና በለሳን ከርቤም ተጭነው ነበር።


ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር።


ሁሉን የሚችል አምላክም ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ከእናንተ ጋር ይሰድድ ዘንድ በዚያ ሰው ፊት ምሕረትን ይስጣችሁ እኔም ልጆቼን እንዳጣሁአጣሁ።


ሰዎቹም በእጅቸው ያችን እጅ መንሻና አጠፌታውን ብር ብንያምንም ወሰዱ ተነሥተውም ወደ ግብፅ ወረዱ፥ በዮሴፍም ፊት ቆሙ።


ዮሴፍም በእኩለ ቀን እስኪገባ ድረስ እነርሱ እጅ መንሻቸው አዘጋጁ ከዚያ እንጀራን እንደሚበሉ ሰምተዋልና።


ዮሴፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእጃቸው ያለው እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀረቡለት ወደ ምድርም ወድቀው ሰገዱለት።


ከእነርሱም እያንዳንዱ በዓመት በዓመቱ ገጸ በረከቱን፥ የብርና የወርቅ ዕቃ፥ ልብስና የጦር መሣሪያ፥ ሽቱም፥ ፈረሶችና በቅሎች እየያዘ ይመጣ ነበር።


“በእኔና በአንተ መካከል በአባቴና በአባትህም መካከል ቃል ኪዳን ጸንቶአል፤ እነሆ፥ ብርና ወርቅ ገጸ በረከት ሰድጄልሃለሁ፤ እርሱ ከእኔ ዘንድ እንዲርቅ ሄደህ ከእስራኤል ንጉሥ ከባኦስ ጋር ያለህን ቃል ኪዳን አፍርስ፤” ብሎ ሰደደ።


ሰሎሞንም ከወንዙ ጀምሮ እስከ ግብጽ ዳርቻ እስከ ፍልስጥኤም ድረስ በመንግሥታት ሁሉ ላይ ነግሦ ነበር፤ ግብርም ያመጡለት ነበር፤ በዕድሜውም ሙሉ ለሰሎሞን ይገዙ ነበር።


አካዝም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብርና ወርቅ ወስዶ ወደ አሦር ንጉሥ ገጸ በረከት አድርጎ ሰደደው።


በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ እንደ ታመመ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ወደ ሕዝቅያስ ላከ።


ንጉሡም አዛሄልን “ገጸ በረከት በእጅህ ወስደህ የእግዚአብሔርን ሰው ልትገናኝ ሂድ፤ በእርሱም አፍ ‘ከዚህ በሽታ እድናለሁን?’ ብለህ እግዚአብሔርን ጠይቅ፤” አለው።


ሄደህ በሱሳ ያሉትን አይሁድ ሁሉ ሰብስብ፥ ለእኔም ጹሙ፥ ሦስት ቀን ሌሊቱንና ቀኑን አትብሉም፥ አትጠጡም፥ እኔና ደንገጥሮቼ ደግሞ እንዲሁ እንጾማለን፥ ምንም እንኳ ያለ ሕግ ቢሆን ወደ ንጉሡ እገባለሁ፥ ብጠፋም እጠፋለሁ።


ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም አገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው አገር ወደ ሰፊይቱና ወደ መልካሚቱ አገር ወደ ከነዓናውያንም ወደ ኬጢያውያንም ወደ አሞራውያንም ወደ ፌርዛውያንም ወደ ኤዊያውያንም ወደ ኢያቡሳውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።


እኅቴ ሙሽራ ሆይ፥ ፍቅርሽ እንዴት መልካም ነው! ፍቅርሽ ከወይን ጠጅ ይልቅ እንዴት ይሻላል! የዘይትሽም መዓዛ ከሽቱ ሁሉ!


ናርዶስ ከቀጋ ጋር፥ የሽቱ ሣርና ቀረፋ፥ ከልዩ ልዩ ዕጣን ጋር፥ ከርቤና እሬት ከክቡር ሽቱ ሁሉ ጋር።


ውዴ ሆይ፥ ፍጠን፥ በቅመም ተራራ ላይ ሚዳቋን ወይም የዋላን እምቦሳ ምሰል።


በገለዓድ የሚቀባ መድኃኒት የለምን? ወይስ በዚያ ሐኪም የለምን? የወገኔ ሴት ልጅ ፈውስ ስለ ምን አልሆነም?


የድዳን ሰዎች ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ ይለውጡ ዘንድ የዝሆን ጥርስና ዞጲ አመጡልሽ።


ይሁዳና የእስራኤል ምድር ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ የሚኒትን ስንዴ ጣፋጭም እንጕቻ፥ ማር ዘይትም በለሳንም ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።


የሳባና የራዕማ ነጋዴዎች እነዚህ ነጋዴዎችሽ ነበሩ፥ በጥሩ ሽቶና በክብር ድንጋይ ሁሉ በወርቅም ስለ አንቺ ሸቀጥ ይነግዱ ነበር።


ነገር ግን እናንተን፦ ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ። እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።


ምክርንም ሊቀበል እምቢ ባለ ጊዜ፦ የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን።


በፀሐዩ ፍሬያት ገናንነት፥ 2 በጨረቃውም መውጣት ገናንነት


አሁንም ባሪያህ ወደ ጌታዬ ያመጣችው ይህ መተያያ ጌታዬን ለሚከተሉ ጕልማሶች ይሰጥ።


ሳኦልም ብላቴናውን፦ እነሆ፥ እንሄዳለን፥ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሰው ምን እናመጣለታለን? እንጀራ ከከረጢታችን አልቆአልና፥ እጅ መንሻም የለንምና ለእግዚአብሔር ሰው የምናመጣለት ምን አለን? አለው።


跟着我们:

广告


广告