Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 42:36 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 አባታቸውን ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፦ ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ ዮሴፍ የለም ስምዖንም የለም ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 አባታቸው ያዕቆብም፣ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጕድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 በዚህ ጊዜ አባታቸው “ልጆቼን ሁሉ እንዳጣ ትፈልጋላችሁን? ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ለመውሰድ ትፈልጋላችሁ፤ በዚህ ሁሉ መከራ የምሠቃየው እኔ ነኝ!” አለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 አባ​ታ​ቸው ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ልጅ አልባ አስ​ቀ​ራ​ች​ሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስም​ዖ​ንም የለም፤ ብን​ያ​ም​ንም ትወ​ስ​ዱ​ብ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 42:36
21 交叉引用  

ሮቤልም አባቱን አለው፦ ወደ አንተ መልሼ ያላመጣሁት እንደ ሆነ ሁለቱን ልጆቼን ግደል እርሱን በእጄ ስጠኝ እኔም ወደ አንተ እመልሰዋለሁ።


ሁሉን የሚችል አምላክም ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ከእናንተ ጋር ይሰድድ ዘንድ በዚያ ሰው ፊት ምሕረትን ይስጣችሁ እኔም ልጆቼን እንዳጣሁአጣሁ።


እርሱም ከታላቁ ጀምሮ እስከ ታናሹ ድረስ በረበራቸው ጽዋውንም በብንያም ዓይበት ውስጥ አገኘው።


እስራኤልም፦ ልጄ ዮሴፍ ገና በሕይወት ከሆነ ይበቃኛል ሳልሞት እንዳየው እሄዳለሁ አለ።


ዮሴፍም ለአባቱና ለወንድሞቹ ለአባቱም ቤተስዎች ሁሉ እንደ ልጆቻቸው መጠን እህል ሰጣቸው።


ሕይወቴ እስትንፋስ እንደ ሆነ አስብ፥ ዓይኔ መልካም ነገርን ከእንግዲህ ወዲህ አያይም።


የነገር ፍጻሜ ከመጀመሪያው ይሻላል፥ ታጋሽም ከትዕቢተኛ ይሻላል።


ስለዚህም የማምለኪያ ዐፀዶችና የፀሐይ ምስሎች ዳግመኛ እንዳይነሡ የመሠዊያውን ድንጋይ ሁሉ እንደ ደቀቀ እንደ ኖራ ድንጋይ ባደረገ ጊዜ፥ እንዲሁ የያዕቆብ በደል ይሰረያል፥ ይህም ኃጢአትን የማስወገድ ፍሬ ሁሉ ነው።


እኔ፦ በሕይወት ዘመኔ መካከል ወደ ሲኦል በሮች እገባለሁ፥ የቀረው ዘመኔ ጐደለብኝ አልሁ።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፥ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የዋይታና የመራራ ልቅሶ ድምፅ በራማ ተሰማ፥ ራሔል ስለ ልጆችዋ አለቀሰች፥ የሉምና ስለ ልጆችዋ መጽናናትን እንቢ አለች።


ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና፦ አንተ እምነት የጎደለህ፥ ስለምን ተጠራጠርህ? አለው።


እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።


እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


ለሰው ሁሉ ከሚሆነው በቀር ምንም ፈተና አልደረሰባችሁም፤ ነገር ግን ከሚቻላችሁ መጠን ይልቅ ትፈተኑ ዘንድ የማይፈቅድ እግዚአብሔር የታመነ ነው፥ ትታገሡም ዘንድ እንድትችሉ ከፈተናው ጋር መውጫውን ደግሞ ያደርግላችኋል።


የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።


ዳዊትም በልቡ፦ አንድ ቀን በሳኦል እጅ እጠፋለሁ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሽ በቀር የሚሻለኝ የለም፥ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፥ እንዲህም ከእጁ እድናለሁ አለ።


跟着我们:

广告


广告