Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 42:28 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ለወንድሞቹም፦ ብሬ ተመለሰችልኝ እርስዋም በዓይበቱ አፍ እነኍት አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ እየተንቀጠቀጡም እርስ በርሳቸው ተባባሉ፦ እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድር ነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 እርሱም ወንድሞቹን፥ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፥ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 እርሱም ለወንድሞቹ “ገንዘቤ ተመልሶልኛል፤ ይኸው በስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት!” ብሎ ነገራቸው። ሁሉም በፍርሃት ተንቀጥቅጠው “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም፥ “ብሬ ተመ​ለ​ሰ​ች​ልኝ፤ እር​ስ​ዋም በዓ​ይ​በቴ አፍ እነ​ኋት” አላ​ቸው። ልባ​ቸ​ውም ደነ​ገጠ፤ እየ​ታ​ወ​ኩም እርስ በር​ሳ​ቸው ተባ​ባሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ረ​ገ​ብን ይህ ምን​ድን ነው?”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 42:28
14 交叉引用  

ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።


ወደ አባታቸውም ወደ ያዕቆብ ወደ ከነዓን ምድር መጡ የደረሰባቸውንም ነገር ሁሉ እንዲህ ብለው አወሩ፦


አባታቸውን ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፦ ልጅ አልባ አስቀራችሁኝ ዮሴፍ የለም ስምዖንም የለም ብንያምንም ትወስዱብኛላችሁ ይህ ሁሉ በእኔ ላይ ደረሰ፤


እርሱም አላቸው፦ ስላም ለእናንተ ይሁን አትፍሩ አምላካችሁና የአባታችሁ አምላክ በዓይበታችሁ የተሰወረ ገንዘብ ሰጣችሁ ብራችሁስ ደርሶኛል።


የማዕዱንም መብል፥ የብላቴኖቹንም አቀማመጥ፥ የሎሌዎቹንም አሠራር፥ አለባበሳቸውንም፥ ጠጅ አሳላፊዎቹንም፥ በእግዚአብሔርም ቤት የሚያሳርገውን መሥዋዕት ባየች ጊዜ ነፍስ አልቀረላትም።


ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከቃሉ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ አልመለሰልኝም።


ብርሃንን ሠራሁ፥ ጨለማውንም ፈጠርሁ፥ ደኅንነትን እሠራለሁ፥ ክፋትንም እፈጥራለሁ፥ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።


ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፥ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፥ አፈረሰ አልራራምም፥ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፥ የሚያስጨንቁሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ።


ሜም። ጌታ ያላዘዘውን የሚልና የሚፈጽም ማን ነው?


በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ ተለይተው በቀሩት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እሰድድባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታሸብራቸዋለች፤ ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።


ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይፈራምን? ወይስ ክፉ ነገር በከተማ ላይ የመጣ እንደ ሆነ ያደረገው እግዚአብሔር አይደለምን?


ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና።


በእነዚያም አሕዛብ መካከል ዕረፍት አታገኝም፥ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ አይሆንም፤ በዚያም እግዚአብሔር ተንቀጥቃጭ ልብ፥ ፈዛዛ ዓይን፥ ደካማም ነፍስ ያመጣብሃል።


跟着我们:

广告


广告