Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 42:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ነገራችሁ ይፈተን ዘንድ ከእናንተ አንዱን ስደዱ፥ ወንድማችሁንም ይዞ ይምጣ እናንተም ታድራችሁ ተቀመጡ ይህ ካልሆነ የፈርዖን ሕይወት ሰላዮች ናችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በሉ፣ ከእናንተ አንዱን ላኩና ወንድማችሁን ይዞ ይመለስ፤ የቀራችሁት ግን የተናገራችሁት ቃል እውነትነቱ እስኪረጋገጥ ድረስ እስር ቤት ትቈያላችሁ። እንደ ተናገራችሁት ካልሆነ ግን፣ በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ ሁላችሁም ሰላዮች ናችሁ” አላቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በሉ፥ ከእናንተ አንዱን ላኩና ወንድማችሁን ይዞ ይመለስ፤ የቀራችሁት ግን የተናገራችሁት ቃል እስኪረጋገጥ ድረስ፥ እስር ቤት ትቆያላችሁ። እንደ ተናገራችሁት ካልሆነ ግን፥ በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ ሁላችሁም ሰላዮች ናችሁ” አላቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከእናንተ አንዱ ሄዶ ወንድማችሁን ያምጣ፤ የተናገራችሁት እውነት መሆኑ ተረጋግጦ ነጻ እስክትለቀቁ ድረስ የቀራችሁት እዚሁ በእስር ቤት ትቈያላችሁ አለበለዚያ ግን በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ እናንተ ሰላዮች ናችሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ያመጣ ዘንድ ከእ​ና​ንተ አን​ዱን ላኩ፤ እና​ንተ ግን እው​ነ​ትን የም​ት​ና​ገሩ ከሆነ ወይም ከአ​ል​ሆነ ነገ​ራ​ችሁ እስ​ኪ​ታ​ወቅ ድረስ ከዚህ ተቀ​መጡ፤ ይህ ከአ​ል​ሆነ ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ሰላ​ዮች ናችሁ።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 42:16
4 交叉引用  

እና ሁላችን የአንድ ሰው ልጆች ነን እኛ እውነተኞች ነን ባሪያዎችህስ ሰላዩች አይደሉም


የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፋ ንግግር ተናገረን የምድሪቱም ሰላዮች አስመሰለን።


የአሞንም ልጆች አለቆች ጌታቸውን ሐኖንን፦ ዳዊት አባትህን አክብሮ ሊያጽናናህ ባሪያዎቹን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ዳዊትስ ከተማይቱን ለመመርመርና ለመሰለል ለማጥፋትም ባሪያዎቹን የላከ አይደለምን? አሉት።


የነዌም ልጅ ኢያሱ፦ ሄዳችሁ ምድሪቱንና ኢያሪኮን እዩ ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ። ሄዱም፥ ረዓብም ወደሚሉአት ጋለሞታ ቤት ገቡ፥ በዚያም አደሩ።


跟着我们:

广告


广告