Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 42:15 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 በዚህ ትፈተናላችሁ ታናሽ ወንድማችሁ ካልመጣ በቀር የፈርዖንን ሕይወት ከዚህ አትወጡም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ታናሽ ወንድማችሁ እዚህ እስካልመጣ ድረስ ከዚህ ንቅንቅ እንደማትሉ በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ ማንነታችሁ የሚረጋገጠውም በዚህ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ታናሽ ወንድማችሁ እዚህ እስካልመጣ ድረስ ከዚህ ንቅንቅ እንደማትሉ በፈርዖን ስም እምላለሁ፤ ማንነታችሁ የሚረጋገጠውም በዚህ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 እንግዲህ ታማኝነታችሁ ተፈትኖ የሚረጋገጠው በዚህ ነው፤ ታናሽ ወንድማችሁ እስከሚመጣ ድረስ እንደማልለቃችሁ በንጉሡ በፈርዖን ስም እምላለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ታናሽ ወን​ድ​ማ​ች​ሁን ከአ​ላ​መ​ጣ​ችሁ በቀር ‘የፈ​ር​ዖ​ንን ሕይ​ወት!’ ከዚህ አት​ወ​ጡም።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 42:15
19 交叉引用  

እርሱም አላቸው፦ አይደለም ነገር ግን የአገሩን ዕራቁትንት ልታዩ መጥታችኍል።


ዮሴፍም አላቸው፦ እናንተ ሰላዮች ናችሁ ብዬ የተናገርኍችሁ ይህ ነው


እውነትን የምትናገሩ ከሆነ ነገራችሁ ይፈተን ዘንድ ከእናንተ አንዱን ስደዱ፥ ወንድማችሁንም ይዞ ይምጣ እናንተም ታድራችሁ ተቀመጡ ይህ ካልሆነ የፈርዖን ሕይወት ሰላዮች ናችሁ።


ታናሹንም ወንድማችሁን ወደ እኔ ይዛችሁ ኑ ነገራችሁም የታመነ ይሆናልና አትሞቱም።


የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፋ ንግግር ተናገረን የምድሪቱም ሰላዮች አስመሰለን።


ታናሹንም ወንድማችሁን አምጡልኝ እውነተኞች እንጂ ሰላዮች አለመሆናችሁንም በዚህ አውቀዋለሁ ወንድማችሁንም እሰጣችኍለሁ እናንተም በምድሩ ትነግዳላችሁ።


ዮሴፍም ወንድሞቹን አይቶ አወቃቸው ተለወጠባቸውም ክፋ ቃልንም ተናገራቸው፦ እናንተ ከወዴት መጣችሁ? አላቸው። እነርሱም፦ ከከነዓን ምድር እህል ልንሸምት የመጣን ነን አሉት።


ይሁዳም እንዲህ አለው፦ ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዪም ብሎ በብርቱ ቃል አስጠነቀቀን።


ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዮም ብሎናልና።


እነርሱም፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ቢሉ የሚምሉት በሐሰት ነው።


በእነዚህ ነገሮች ይቅር የምልሽ እንዴት አድርጌ ነው? ልጆችሽ ትተውኛል አማልክትም ባልሆኑ ምለዋል፥ ካጠገብኋቸውም በኋላ አመነዘሩ በጋለሞቶቹም ቤት ተሰበሰቡ።


አምላክህን እግዚአብሔርን ፍራ፤ እርሱንም አምልክ፤ በስሙም ማል።


ከሁሉም በፊት፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በሰማይ ቢሆን በምድርም ቢሆን በሌላ መሐላም ቢሆን በምንም አትማሉ፤ ነገር ግን ከፍርድ በታች እንዳትወድቁ ነገራችሁ አዎን ቢሆን አዎን ይሁን፥ አይደለምም ቢሆን አይደለም ይሁን።


እርስዋም አለች፦ ጌታዬ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ! ጌታ ሆይ፥ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ በዚህ በአንተ ዘንድ ቆማ የነበረች ሴት እኔ ነኝ።


ሳኦልም ዳዊትን ወደ ፍልስጥኤማዊው ሲወጣ ባየው ጊዜ ለሠራዊቱ አለቃ ለአበኔር፦ አበኔር ሆይ፥ ይህ ብላቴና የማን ልጅ ነው? አለው። አበኔርም፦ ንጉሥ ሆይ፥ በሕያው ነፍስህ እምላለሁ፥ አላውቅም አለ።


ዳዊትም፦ እኔ በፊትህ ሞገስ እንዳገኘሁ አባትህ በእውነት ያውቃል፥ እርሱም፦ ዮናታን እንዳይከፋው አይወቅ ይላል፥ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ያህል ቀርቶአል ብሎ ማለ።


跟着我们:

广告


广告