Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 41:43 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው አዋጅ ነጋሪም፦ ስገዱ እያለ በፊት በፊት ይጮኽ ነበር እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ተሾመ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 በማዕርግ ከርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፣ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፣ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 በማዕረግ ከእርሱ ሁለተኛ ሰው አድርጎ፥ በሠረገላ ላይ አስቀመጠው። ሰዎችም በፊቱ፥ “እጅ ንሡ” እያሉ ይጮኹ ነበር፤ በዚህ ሁኔታም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ሾመው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 በንጉሡ ሁለተኛ ሠረገላ ላይ እንዲቀመጥ አደረገው፤ የንጉሡም የክብር ዘብ ከፊት ፊት እየሄደ “እጅ ንሡ! እጅ ንሡ!” ይል ነበር፤ ዮሴፍ በግብጽ ምድር ላይ አስተዳዳሪ ሆኖ የተሾመው በዚህ ዐይነት ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 የእ​ር​ሱም በም​ት​ሆን በሁ​ለ​ተ​ኛ​ይቱ ሰረ​ገላ አስ​ቀ​መ​ጠው፤ ስገዱ እያ​ለም በፊት በፊቱ አዋጅ ነጋሪ እን​ዲ​ሄድ አደ​ረገ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ላይም ሾመው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 41:43
16 交叉引用  

ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ በዮሴፍ እጅም አደረገው ነጭ የተልባ እግር ልብስንም አለበሰው በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤


ፈርዖንም ዮሴፍን አለው፦ እኔ ፈርዖን ነኝ በግብፅ አገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁንም እግሩንም አያንሣ።


የአገሩ ጌታ የሆነው ሰው በክፋ ንግግር ተናገረን የምድሪቱም ሰላዮች አስመሰለን።


የአገሩም ጌታ ያ ስው እንዲህ አለን፦ የታመናችሁ ስዎች ከሆናችሁ በዚህ አውቃለሁ አንደኛውን ወንድማችሁን ከእኔ ጋር ተውት ለቤታችሁም ራብ እህልን ወስዳችሁ ሂዱ፤


ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ሰገዱለት።


እንዲህም ብለው ነገሩት፦ ዮሴፍ ገና በሕይወት ነው እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ገዥ ሆኖአል። ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ አላመናቸውም ነበርና።


አሁንም እናንተ ወደዚህ የላካችሁኝ አይደላችሁም እግዚአብሔር ላከኝ እንጂ ለፈርዖንም እንደ አባት አደረገኝ በቤቱምም ሁሉ ላይ ጌታ በግብፅ ምድርም ሁሉ ላይ አለቃ አደረገኝ።


ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው፦ እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን አሉት።


ሰረጎሎችም ፈረሶኞችም ከእርሱ ጋር ወጡ ሠራዎቱም እጅግ ብዙ ነበረ።


አይሁዳዊውም መርዶክዮስ ለንጉሡ ለአርጤክስስ በማዕረግ ሁለተኛ ነበረ፥ በአይሁድም ዘንድ የከበረ፥ በብዙ ወንድሞችም ዘንድ የተወደደ፥ ለሕዝቡም መልካምን የፈለገ፥ ለዘሩም ሁሉ በደኅና የተናገረ ነበረ።


ንጉሡም ስለ እርሱ እንዲሁ አዝዞ ነበርና በንጉሡ በር ያሉት የንጉሡ ባሪያዎች ሁሉ ተደፍተው ለሐማ ይሰግዱ ነበር። መርዶክዮስ ግን አልተደፋም፥ አልሰገደለትም።


ምንም በመንግሥቱ አገር ደግሞ ችግረኛ ሆኖ ቢወለድ፥ ከግዞቱ ቤት ወደ መንግሥት ወጥቶአልና።


ንጉሡም ዳንኤልን ከፍ ከፍ አደርገው፥ ብዙም ታላቅ ስጦታ ሰጠው፥ በባቢሎንም አውራጃ ሁሉ ላይ ሾመው፥ በባቢሎንም ጠቢባን ሁሉ ላይ ዋነኛ አለቃ አደረገው።


ከመከራውም ሁሉ አወጣው፥ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖንም ፊት ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፥ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይም ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።


ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥


跟着我们:

广告


广告