Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 41:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከሁለት ዓመት በኍላም ፈርዖን ሕልምን አየ፥ እነሆም በወንዙ ዳር ቆሞ ነበረ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለመ፤ በሕልሙም፣ በአባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ድፍን ሁለት ዓመት ካለፈ በኋላ ፈርዖን ሕልም ዐለመ፤ በሕልሙም፥ በዐባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከሁለት ዓመት በኋላ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሕልም አየ፤ እርሱ በሕልሙ በዓባይ ወንዝ ዳር ቆሞ ነበር፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከሁ​ለት ዓመት በኋ​ላም ፈር​ዖን ሕል​ምን አየ፤ እነ​ሆም፥ በወ​ንዙ ዳር ቆሞ ነበር።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 41:1
21 交叉引用  

እግዚአብሔርም ሌሊት በሕልም ወደ አቢሜሌክ መጣ፥ እንዲህም አለው፤ እነሆ አንተ ስለ ወሰድሃት ሴት ምውት ነህ እርስዋ ባለ ባል ናትና።


ሕልምም አለመ፤ እነሆም መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር።


ላባም፦ በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።


እርሱም ያለውን ሁሉ ይዞ ኮበለለ ተነሥቶም ወንዙን ተሻገረ፥ ፊቱንም ወደ ገለዓድ ተራራ አቀና።


የጠጅ አሳላፊዎች አለቃ ግን ዮሴፍን አላሰበውም ረሳው እንጂ።


በግዞት ቤት የነበሩት የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊና እንጀራ አበዛ ሁለቱም በአንዲት ሌሊት እንደ ሕልሙ ትርጓሜ እየራሳቸው ሕልምን አለሙ።


እነሆም መልካቸው ያማረ ሥጋቸውም የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ በውኃውም ዳር በመስኩ ይስማሩ ነበር።


በዚያም ሌሊት እንቅልፍ ከንጉሡ ሸሸ፥ የዘመኑንም ታሪክ መጽሐፍ ያመጡ ዘንድ አዘዘ፥ በንጉሡም ፊት ተነበበ።


ፈርዖንም፦ “የሚወለደውን ወንድ ልጅ ሁሉ ወደ ወንዝ ጣሉት፤ ሴትን ልጅ ሁሉ ግን በሕይወት አድኑአት፤” ብሎ ሕዝቡን ሁሉ አዘዘ።


እንዲህም ይሆናል፤ እነዚህን ሁለት ምልክቶች ባያምኑ ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከወንዙ ውኃን ውሰድ፤ በደረቁም መሬት ላይ አፍስሰው፤ ከወንዙም የወሰድኸው ውኃ በደረቁ መሬት ላይ ደም ይሆናል።”


ውኆችም ከባሕር ይደርቃሉ፥ ወንዙም ያንሳል ደረቅም ይሆናል።


እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የምትተኛና፦ ወንዙ የእኔ ነው ለራሴም ሠርቼዋለሁ የምትል ታላቅ አዞ፥ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ፥ እነሆ፥ በአንተ ላይ ነኝ።


የግብጽም ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፥ አንተ፦ ወንዙ የእኔ ነው የሠራሁትም እኔ ነኝ ብለሃልና።


እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ፦ ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ ብላ ላከችበት።


ትወርሳት ዘንድ የምትገባባት ምድር፥ በአትክልት ስፍራ እንደሚዘሩ ዘርህን እንደዘራህባት፥ በእግርህም እንዳጠጣሃት፥ እንደ ወጣህባት እንደ ግብፅ ምድር አይደለችም።


跟着我们:

广告


广告