Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 40:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በጌታው ቤት ከእርሱ ጋር በግዞት የነበሩትንም የፈርዖንን ሹማምት እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፦ እናንተ ዛሬ ስለ ምን አዝናችኍል?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህም፣ “ምነው ዛሬስ ፊታችሁ ላይ ሐዘን ይነበባል?” በማለት ዐብረውት በጌታው ግቢ የታሰሩትን የፈርዖን ሹማምት ጠየቃቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ስለዚህም፥ “ምነው ዛሬስ ፊታችሁ ላይ ኀዘን ይነበባል?” በማለት አብረውት በጌታው ግቢ የታሰሩትን የፈርዖን ሹማምንት ጠየቃቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ዛሬ በፊታችሁ ላይ ሐዘን የሚታየው ለምንድን ነው?” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 በጌ​ታው ቤት ከእ​ርሱ ጋር በግ​ዞት የነ​በ​ሩ​ት​ንም የፈ​ር​ዖን ሹሞች እን​ዲህ ብሎ ጠየ​ቃ​ቸው፥ “እና​ንት ዛሬ ስለ​ምን አዝ​ና​ች​ኋል?”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 40:7
7 交叉引用  

ዮሴፍም ማልዶ ወደ እነርሱ ገባ እነሆም አዝነው አያቸው።


ሦስት ቀን ያህል በግዞት ቤት ጨመራቸው።


እርሱም፦ የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን? አለው። አምኖንም፦ የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ አለው።


ንጉሡም፦ “ሳትታመም ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኅዘን ነው እንጂ ሌላ ነገር አይደለም” አለኝ። እጅግም ብዙ አድርጌ ፈራሁ።


እርሱም፦ እየጠወለጋችሁ ስትሄዱ፥ እርስ በርሳችሁ የምትነጋገሩአቸው እነዚህ ነገሮች ምንድር ናቸው? አላቸው።


እርሱም፦ የሠራኋቸውን አማልክቴን ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችኋል፥ ሌላ ምን አለኝ? እናንተስ፦ ምን ሆነሃል እንዴት ትሉኛላችሁ? አለ።


ባልዋም ሕልቃና፦ ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትቀምሺም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከአሥር ልጆች አልሻልልሽምን? አላት።


跟着我们:

广告


广告