Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 40:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 በሦስተኛውም ቀን ፈርዖን የተወለደበት ቀን ነበረ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ከፍ አደረገ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 በሦስተኛውም ቀን የፈርዖን የልደት በዓል ነበረ፤ ለሹማምቱም ሁሉ ግብር አበላ። በዚያ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምቱ ባሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 በሦስተኛውም ቀን የፈርዖን የልደት በዓል ነበረ፤ ለሹማምንቱም ሁሉ ግብር አበላ። በዚያኑ ዕለትም የመጠጥ አሳላፊዎችን አለቃና የእንጀራ ቤት አዛዡን ሹማምንቱ ካሉበት ከእስር ቤት አወጣቸው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለ ነበረ ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ቀን የወይን ጠጅ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኀላፊው ከእስር ቤት ወጥተው በመኳንንቱ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ፈር​ዖን የተ​ወ​ለ​ደ​በት ዕለት ነበር፤ ለሠ​ራ​ዊ​ቱም ሁሉ ግብር አደ​ረገ፤ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎ​ቹን አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎ​ቹን አለቃ በአ​ሽ​ከ​ሮቹ መካ​ከል ዐሰበ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 40:20
14 交叉引用  

ሕፃኑም አደገ ጡትንም ከመጥባት ተቋረጠ፤ አብርሃምም ይስሐቅን ጡት ባስጣለበት ቀን ትልቅ ግብዣን አደረገ።


ወደ ቀደመው ሹመትህም ይመልስሃል ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታድርግ እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሥርዓትም የፈርዓንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ።


እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ከፍ ያደርጋል፥ በእንጨትም ላይ ይስቅልሃል ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።


ሰሎሞንም ነቃ፤ እነሆም፥ ሕልም ነበረ፤ ወደ ኢየሩሳሌምም መጥቶ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አሳረገ፤ የደኅንነትንም መሥዋዕት አቀረበ፤ ለባሪያዎቹም ሁሉ ግብዣ አደረገ።


እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማከረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ ሰባተኛው ቀን የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪንን ከወህኒ አወጣው፤


በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ለባለምዋሎቹና ለአገልጋዮቹ ሁሉ ግብዣ አደረገ፥ የፋርስና የሜዶን ታላላቆች ሁሉ፥ የየአገሩ አዛውንትና ሹማምት፥ በፊቱ ነበሩ፥


ከዚያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ።


እንዲህም ሆነ፥ የይሁዳ ንጉሥ ዮአኪን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት በአሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሀያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴክ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የዮአኪንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ ከወህኒም አወጣው፥


ነገር ግን ሄሮድስ የተወለደበት ቀን በሆነ ጊዜ፥ የሄሮድያዳ ልጅ በመካከላቸው ዘፈነች ሄሮድስንም ደስ አሰኘችው፤


ከብዙ ዘመንም በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቆጣጠራቸው።


በደስታም ይሰማው ነበር። ሄሮድስም በተወለደበት ቀን ለመኳንንቱና ለሻለቆቹ ለገሊላም ሹማምንት ግብር ባደረገ ጊዜ ምቹ ቀን ሆነላትና


跟着我们:

广告


广告