Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 40:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈርዖን ራስህን ከፍ ያደርጋል፥ በእንጨትም ላይ ይስቅልሃል ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 በሦስት ቀን ውስጥ ፈርዖን ከእስር ቤት ያወጣሃል፤ በዕንጨትም ላይ ይሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ፈርዖን ከዚህ እስር ቤት አውጥቶ ራስህን ካስቈረጠ በኋላ በእንጨት ላይ ያሰቅልሃል፤ ወፎችም ሥጋህን ይበሉታል።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እስከ ሦስት ቀን ድረስ ፈር​ዖን ራስ​ህን ይቈ​ር​ጥ​ሃል፤ በዕ​ን​ጨ​ትም ላይ ይሰ​ቅ​ል​ሃል፤ የሰ​ማይ ወፎ​ችም ሥጋ​ህን ይበ​ሉ​ታል።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 40:19
17 交叉引用  

ወደ ቀደመው ሹመትህም ይመልስሃል ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታድርግ እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሥርዓትም የፈርዓንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ።


በላይኛውም መሶብ ፈርዖን ከሚበላው ከጋጋዎች ሥራ ሁሉ ነበረበት፤ ወፎችም በራሴ ላይ ከመሶቡ ይበሉ ነበር።


ዮሴፍም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዚህ ትርጓሜው ይህ ነው ሦስት መሶብ ሦስት ቀን ነው።


በሦስተኛውም ቀን ፈርዖን የተወለደበት ቀን ነበረ ለሠራዊቱም ሁሉ ግብር አደረገ የጠጅ አሳላፊዎቹን አለቃና የእንጀራ አበዛዎቹን አለቃ በአሽከሮቹ መካከል ከፍ አደረገ።


የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ ሰቀለው ዮሴፍ እንደተረጎመላቸው።


እንዲህም ሆነ እንደ ተረጎመልን እንደዚያው ሆነ እኔ ወደ ሹመቴ ተመለስሁ እርሱም ተሰቀለ።


የኢዮሄልም ልጅ ሪጽፋ ማቅ ወስዳ ከመከር ወራት ጀምሮ ዝናብ ከሰማይ እስኪዘንብ ድረስ በድንጋይ ላይ ዘረጋችው በቀንም ወፎች በሌሊትም አራዊት ያርፉባቸው ዘንድ አልተወችም።


ካሰበው ሰው ልጆች ሰባት ሰዎች አሳልፈህ ስጠንና ከእግዚአብሔር በተመረጠው በሳኦል አገር በጊብዓ ለእግዚአብሔር እንሰቅላቸዋለን አሉት። ንጉሡም፦ እሰጣችኋለሁ አለ።


አንተና ጭፍሮችህ ሁሉ ከአንተም ጋር ያሉ ሕዝብ በእስራኤል ተራሮች ላይ ትወድቃላችሁ፥ ለሚናጠቁ ወፎች ሁሉና ለምድር አራዊትም መብል አድርጌ እሰጥሃለሁ።


የእግዚአብሔርን ምክር ሁሉ ነግሬአችኋለሁና፥ ምንም አላስቀረሁባችሁም።


በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤


ከዚህም በኋላ መትተው ገደሉአቸው፥ በአምስቱም ዛፎች ላይ ሰቀሉአቸው፥ እስከ ማታም ድረስ በዛፎቹ ተሰቅለው ቈዩ።


የጋይንም ንጉሥ እስከ ማታ ድረስ በዛፍ ላይ ሰቀለው፥ ፀሐይም በገባች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፥ ሬሳውንም ከዛፍ አወረዱት፥ በከተማይቱም በር አደባባይ ጣሉት፥ በላዩም እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት።


ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፦ ወደ እኔ ና፥ ሥጋህንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ አለው።


እግዚአብሔር ዛሬ አንተን በእጄ አሳልፎ ይሰጣል፥ እመታህማለሁ፥ ራስህንም ከአንተ አነሣዋለሁ፥ የፍልስጥኤማውያንንም ሠራዊት ሬሶች ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት ዛሬ እሰጣለሁ። ይኸውም ምድር ሁሉ በእስራኤል ዘንድ አምላክ እንዳለ ታውቅ ዘንድ፥


跟着我们:

广告


广告