Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 40:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ነገር ግን በጎ ነገር በተደረግልህ ጊዜ እኔን አስበኝ ምሕረትንም አድርግልኝ የእኔንም ነገር ለፈርዖን ነግረህ ከዚህ ቤት አውጣኝ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 እንግዲህ፣ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፣ እኔን ዐስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እንግዲህ፥ በጎ ነገር በገጠመህ ጊዜ፥ እኔን አስበህ ቸርነት አድርግልኝ፤ ስለ እኔም ለፈርዖን ንገርልኝ፤ ከዚህም እስር ቤት አስወጣኝ፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ነገር ግን ሁሉ ነገር በተቃናልህ ጊዜ እኔን አስታውሰህ እርዳኝ፤ ለፈርዖንም አሳስበህ ከእዚህ ከእስር ቤት እንድወጣ አድርገኝ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ነገር ግን በጎ ነገር በተ​ደ​ረ​ገ​ልህ ጊዜ እኔን ዐስ​በኝ፤ ምሕ​ረ​ት​ንም አድ​ር​ግ​ልኝ፤ ስለ እኔም ለፈ​ር​ዖን አሳ​ስ​በህ ከዚህ እስር ቤት አው​ጣኝ፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 40:14
9 交叉引用  

ወደ ቀደመው ሹመትህም ይመልስሃል ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታድርግ እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሥርዓትም የፈርዓንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ።


የዚያን ጊዜ የጠጅ አሳላፈዎቹ አለቃ እንዲህ ብሎ ለፈርዖን ተናገረ፦ እኔ ኃጢአቴን ዛሬ አስባለሁ፤


ዳዊትም፦ ስለ ዮናታን ቸርነት አደርግለት ዘንድ ከሳኦል ቤት አንድ ሰው ቀርቶአልን? አለ።


ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ ቀርበውኛልና ለገለዓዳዊው ለቤርዜሊ ልጆች መልካም ቸርነት አድርግላቸው፤ በማዕድህም ከሚበሉት መካከል ይሁኑ።


ኢየሱስንም፦ ጌታ ሆይ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ አለው።


ባሪያ ሆነህ ተጠርተህ እንደ ሆነ አይገድህም፤ አርነት ልትወጣ ቢቻልህ ግን አርነትን ተቀበል።


አሁንም፥ እባካችሁ፥ በእግዚአብሔር ማሉልኝ፥ በእውነትም ምልክት ስጡኝ፥ እኔ ለእናንተ ቸርነት እንደ ሠራሁ እናንተ ደግሞ ለአባቴ ቤት ቸርነት እንድትሠሩ፥


አንተ በከንቱ ደም እንዳላፈሰስህ፥ በገዛ እጅህም እንዳልተሳካልህ ይህ ዕንቅፋትና የሕሊና ጸጸት በጌታዬ አይሆንልህም፥ እግዚአብሔርም ለጌታዬ በጎ ባደረገልህ ጊዜ፥ ባሪያህን አስብ።


跟着我们:

广告


广告