Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 40:1 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከዚህ ነገር በኍላም እንዲህ ሆነ የግብፅ ንጉሥ የጠጅ አሳላፊና የእንጀራ አበዛ ጌታቸውን የግብፅ ንጉሥን በደሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህም በኋላ የግብጽ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊና እንጀራ ቤቱ ጌታቸውን የግብጽን ንጉሥ በደሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚህም በኋላ የግብጽ ንጉሥ የመጠጥ አሳላፊና እንጀራ ቤቱ ጌታቸውን የግብጽን ንጉሥ በደሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ይህ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የግብጽ ንጉሥ ፈርዖን የወይን ጠጅ አሳላፊና የእንጀራ ቤት ኀላፊ ንጉሡን የሚያሳዝን በደል ፈጸሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚህ ነገር በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ የግ​ብፅ ንጉሥ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ጌታ​ቸ​ውን የግ​ብፅ ንጉ​ሥን በደሉ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 40:1
10 交叉引用  

የዘለላዋም ፍሬ በሰለ የፈርዖን፥ ጽዋ በእጄ ነበረ ፍሬውንም ወስጄ በፈርዖን ጽዋ ጨመቅሁት ጽዋውንም ለፈርዖን በእጁ ሰጠሁት።


ወደ ቀደመው ሹመትህም ይመልስሃል ጠጅ አሳላፊ በነበርህበት ጊዜ ስታድርግ እንደ ነበረው እንደ ቀድሞው ሥርዓትም የፈርዓንን ጽዋ በእጁ ትሰጣለህ።


የእንጀራ አበዛቹ አለቃም ሕልሙን በመልካም እንደ ተረጎመ ባየ ጊዜ ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ እኔም ደግሞ ሕልም አይቼ ነበር እነሆም ሦስት መሶብ ነጭ እንጀራ በራሴ ላይ ነበረ፤


ፈርዖንም በሁለቱ ሹማምቱ በጠጅ አሳላፊዎቹ አለቃና በእንጀራ አበዛዎቹ አለቃ ላይ ተቆጣ፤


በግዞት ቤት የነበሩት የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊና እንጀራ አበዛ ሁለቱም በአንዲት ሌሊት እንደ ሕልሙ ትርጓሜ እየራሳቸው ሕልምን አለሙ።


የዚያን ጊዜ የጠጅ አሳላፈዎቹ አለቃ እንዲህ ብሎ ለፈርዖን ተናገረ፦ እኔ ኃጢአቴን ዛሬ አስባለሁ፤


ጌታ ሆይ፥ ጆሮህ የባሪያህን ጸሎት፥ ስምህንም ይፈሩ ዘንድ የሚወድዱትን፥ የባሪያዎችህን ጸሎት ያድምጥ፤ ዛሬም ለባሪያህ አከናውንለት፤ በዚህም ሰው ፊት ምሕረትን ስጠው።” እኔም ለንጉሡ ጠጅ አሳላፊው ነበርሁ።


በዚያም ሌሊት እንቅልፍ ከንጉሡ ሸሸ፥ የዘመኑንም ታሪክ መጽሐፍ ያመጡ ዘንድ አዘዘ፥ በንጉሡም ፊት ተነበበ።


跟着我们:

广告


广告