Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኽል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ምንድን ነው ያደረግኸው? የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታም ቃየልን እንዲህ አለው፥ “ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔርም ቃየልን እንዲህ አለው፤ “ምን አደረግህ? የፈሰሰው የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለው፥ “ቃየል! ምን አደ​ረ​ግህ? የወ​ን​ድ​ምህ የአ​ቤል የደሙ ድምፅ ከም​ድር ወደ እኔ ይጮ​ሃል።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 4:10
24 交叉引用  

እግዚአብሔርም አለ የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥


እግዚአብሔር አምላክም ሴቲቱን፦ ይህ ያደረግሽው ምንድር ነው? አላት። ሴቲቱም አለች፦ እባብ አሳተኝና በላሁ።


ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ ከስውም እጅ ከስው ወንድም እጅ፤ የስውን ነፍስ እሻለሁ።


‘በእውነት የናቡቴንና የልጆቹን ደም ትናንትና አይቻለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር፤ በዚህም እርሻ እመልስብሃለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።’ ስለዚህ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል ወስደህ በእርሻው ውስጥ ጣለው።”


በዚያም ዖዴድ የተባለ የእግዚአብሔር ነቢይ ነበረ፤ ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ጭፍራ ሊገናኘው ወጣ፤ እንዲህም አላቸው “እነሆ፥ የአባቶቻችሁ አምላክ እግዚአብሔር ይሁዳን ስለ ተቍጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው፤ እናንተም ወደ ሰማይ በሚደርስ ቍጣ ገደላችኋቸው።


ምድር ሆይ፥ ደሜን አትክደኚ፥ ለጩኸቴም ማረፊያ አይሁን።


ከከተማውና ከገዛ ቤቶቻቸው ይባረራሉ፥ የልጆችም ነፍስ ለእርዳታ ትጮኻለች፥ እግዚአብሔር ግን ስንፍናቸውን አይመለከትም።


እግዚአብሔርም አለ፦ “በግብፅ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፤ ከአስገባሪዎቻቸውም የተነሣ ጩኸታቸውን ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።


የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፥ የደስታውም አትክልት የይሁዳ ሰዎች ናቸው፥ ፍርድን ተስፋ ያደርግ ነበር፥ እነሆም፥ ደም ማፍሰስ ሆነ፥ ጽድቅንም ይተማመን ነበር፥ እነሆም፥ ጩኸት ሆነ።


ደም ምድሪቱን ያረክሳታልና የምትኖሩባትን ምድር አታርክሱአት፤ በደም አፍሳሹ ደም ካልሆነ በቀር ምድሪቱ ከፈሰሰባት ደም አትነጻም።


ጴጥሮስም፦ “ሐናንያ ሆይ፥ መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ?


ጴጥሮስም፦ “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለ ምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው አንቺንም ያወጡሻል” አላት።


አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር የተገደለ ሰው በሜዳ ወድቆ ቢገኝ፥


አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፥ በዚህም፥ እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደ ሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።


የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።


እነሆ፥ እርሻችሁን ያጨዱት የሠራተኞች ደመወዝ በእናንተ ተቀምቶ ይጮኻል፥ የአጫጆችም ድምፅ ወደ ጌታ ፀባዖት ጆሮ ገብቶአል።


ኢያሱም አካንን፦ ልጄ ሆይ፥ ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፥ ያደረግኸውንም ንገረኝ፥ አትሸሽገኝ አለው።


ሳሙኤልም፦ ያደረግኸው ምንድር ነው? አለ። ሳኦልም፦ ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በቀጠሮው እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማክማስ እንደ ተሰበሰቡ አየሁ፥


跟着我们:

广告


广告