Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 38:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 አውናንም ዘሩ ለእርሱ እንዳይሆን አወቀ ወደ ወንድሙ ሚስት በገባ ጊዜ ለወንድሙ ዘር እንዳይስጥ ዘሩን በምድር ያፈስሰው ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፣ ከወንድሙ ሚስት ጋራ ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወልድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስስ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 አውናን ግን የሚወለደው ልጅ የእርሱን ስም የሚያስጠራ እንደማይሆን ስላወቀ፥ ከወንድሙ ሚስት ጋር ሩካቤ ሥጋ በፈጸመ ቍጥር የወንድሙንም ስም የሚያስጠራ ልጅ እንዳይወለድ ዘሩን በምድር ላይ ያፈስ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ኦናን የሚወለዱት ልጆች የእርሱ ያለመሆናቸውን በማወቁ ወደ ወንድሙ ሚስት ሲገባ ዘሩን ወደ ምድር ያፈሰው ነበር፤ በዚህ ዐይነት በወንድሙ ስም ልጆች እንዳይወለዱ አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 አው​ና​ንም ዘሩ ለእ​ርሱ እን​ዳ​ይ​ሆን ዐወቀ፤ ወደ ወን​ድሙ ሚስ​ትም በገባ ጊዜ ለወ​ን​ድሙ ዘር እን​ዳ​ይ​ተካ ዘሩን በም​ድር ያፈ​ስ​ሰው ነበር።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 38:9
11 交叉引用  

ይህም ሥራው በእግዚአብሔር ዘንድ ክፋ ሆነበት፥ እርሱንም ደግሞ ቀሠፈው።


ሰነፉን ሰው ቍጣ ይገድለዋል፥ ሰነፉንም ቅንዓት ያጠፋዋል።


ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ፥ ከእርስዋም ጋር ይኑር።


የምዋቹ ስም ከእስራኤል ዘንድ እንዳይጠፋ ከእርስዋ የሚወለደው በኩር ልጅ በሞተው በወንድሙ ስም ይጠራ።


እኛ ደግሞ አስቀድመን የማናስተውል ነበርንና፤ የማንታዘዝ፥ የምንስት፥ ለምኞትና ለልዩ ልዩ ተድላ እንደ ባሪያዎች የምንገዛ፥ በክፋትና በምቀኝንት የምንኖር፥ የምንጣላ፥ እርስ በርሳችን የምንጠላላ ነበርን።


ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ።


ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።


ወይስ መጽሐፍ፦ በእኛ ዘንድ ያሳደረው መንፈስ በቅንዓት ይመኛል ያለው በከንቱ እንደ ተናገረ ይመስላችኋልን?


ኑኃሚንም አለች “ልጆቼ ሆይ! ተመለሱ፤ ለምን ከእኔ ጋር ትሄዳላችሁ? ባሎቻችሁ የሚሆኑ ልጆች በሆዴ አሉኝን?


ደግሞም የምዋቹ ስም ከወንድሞቹ መካከል ከአገርም ደጅ እንዳይጠፋ፥ የምዋቹን ስም በርስቱ ላይ እንዳስነሣ የመሐሎንን ሚስት ሞዓባዊቱን ሩትን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ወሰድሁአት፤ እናንተም ዛሬ ምስክሮች ናችሁ፤” አላቸው።


跟着我们:

广告


广告