Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 37:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበርና እነሆም የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እኛ ሁላችን በዕርሻ ውስጥ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ በድንገት ተነሥታ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእናንተም ነዶዎች ዙሪያዋን ከብበው ለእኔ ነዶ ሰገዱላት።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 እነሆ እኛ በእርሻ መካከል ነዶ ስናስር ነበር፥ እነሆም፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፥ የእናንተም ነዶች በዙሪያ ከብበው እነሆ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እኛ ሁላችን በእርሻ ውስጥ የስንዴ ነዶ እናስር ነበር፤ የእኔ ነዶ ተነሣና ቀጥ ብሎ ቆመ፤ የእናንተ ነዶዎች ዙሪያውን ተሰብስበው ለእኔ ነዶ ሰገዱለት።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 እነሆ፥ እኛ በእ​ርሻ መካ​ከል ነዶ ስና​ስር ነበ​ርና፥ እነሆ፥ የእኔ ነዶ ቀጥ ብላ ቆመች፤ የእ​ና​ን​ተም ነዶ​ዎች በዙ​ርያ ከብ​በው እነሆ፥ ለእኔ ነዶ ሰገዱ።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 37:7
12 交叉引用  

ለወንድሞችህ ጌት ሁን የእናትህም ልጆች ይስገዱልህ የሚረግምህ እርሱ ርጉም ይሁን የሚባርክህም ቡሩም ይሁን።


እርሱ አላቸው፦ እኔ ያለምሁትን ሕልም ስሙ፤


ዮሴፍም በምድር ላይ ገዥ ነበረ እርሱም ለምድር ሕዝብ ሁሉ ይሸጥ ነበር የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ሰገዱለት።


ዮሴፍም ስለ እነርሱ አይቶት የነበረውን ሕልም አሰበ። እንዲህም አላቸው፦ እናንተ ሰላዮች ናችሁ የምድሩን ዕራቁት ልታዩ መጥታችኍል።


ዮሴፍም ወደ ቤቱ በገባ ጊዜ በእጃቸው ያለው እጅ መንሻ በቤት ውስጥ አቀረቡለት ወደ ምድርም ወድቀው ሰገዱለት።


እነርሱ አሉት፦ ባሪያህ አባታችን ደኅና ነው ገና በሕወይት አለ፤ አጎንብሰውም ሰገዱለት።


ይሁዳም ከወንድሞቹ ጋር ወደ ዮሴፍ ገባ እርሱም ገና ከዚያው ነበረ፤ በፊቱም በምድር ላይ ወደቁ።


ይሁዳም ወደ እርሱ ቀረበ እንዲህም አለ፦ ጌታዬ ሆይ እኔ ባርያን በጌታዬ ጆሮ አንዲት ቃልን እንድናገር እለምናለሁ እኔንም ባሪያህን አትቆጣኝ አንተ እንደ ፈርዖን ነህና።


ጌታዬ ባሪያዎቹን፦ አባት አላችሁን ወይስ ወንድም? ብሎ ጠየቀ።


ዮሴፍም ይህን ሲሉት አለቀሰ። ወንድሞቹ ደግሞ መጡ በፊቱም ሰግደው፦ እነሆ እኛ ለአንተ ባሪያዎችህ ነን አሉት።


ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥


እርሱም የአካሉ ማለት የቤተ ክርስቲያን ራስ ነው፤ እርሱም በሁሉ ፊተኛ ይሆን ዘንድ፥ መጀመሪያ ከሙታንም በኵር ነው።


跟着我们:

广告


广告