Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 34:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከምድረ በዳ መጡ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ስንፍናን ስላደረገ አዘኑ እጅግም ተቈጡ እንዲህ አይደረግምን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የያዕቆብ ወንዶች ልጆችም የተፈጸመውን ድርጊት እንደ ሰሙ ወዲያውኑ ከመስክ መጡ፤ ሴኬም መደረግ የማይገባውን አስነዋሪ ነገር በእስራኤል ላይ በመፈጸም፣ የያቆብን ልጅ ስለ ደፈረ ዐዘኑ፤ ክፉኛም ተቈጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የያዕቆብም ልጆች ይህንን በሰሙ ጊዜ ከመስክ መጡ፥ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፥ እንዲህ አይደረግምና እጅግም ተቈጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ልክ በዚያኑ ጊዜ የያዕቆብ ልጆች ከተሰማሩበት መጡ፤ ስለ ተፈጸመው ድርጊት በሰሙ ጊዜ እጅግ ደነገጡ፤ ይህ ነገር መደረግ ስላልነበረበት ሴኬም የያዕቆብን ልጅ በመድፈር የእስራኤልን ሕዝብ በማዋረዱም እጅግ ተቈጡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ከም​ድረ በዳ መጡ፤ ይህ​ንም በሰሙ ጊዜ ፈጽ​መው ደነ​ገጡ፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጅ በመ​ተ​ኛቱ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ኀፍ​ረ​ትን ስላ​ደ​ረገ አዘኑ፤ እጅ​ግም ተቈጡ፤ እን​ዲህ አይ​ደ​ረ​ግ​ምና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 34:7
27 交叉引用  

አቢሜሌክም አብርሃምን ጠርቶ አለው፤ ይህ ያደረግህብን ምንድር ነው? ምንስ ክፉ ሠራሁብህ? በእኔና በመንግሥቴ ላይ ትልቅ ኃጢአት አውርደሃልና የማይገባ ሥራ በእኔ ሠራህብኝ።


የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ ወጣ።


ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦ ልጄ ሴኬም በልጃችሁ ፍቅር ልቡ ተነድፎአልና ሚስት እንድትሆነው እባካችሁ እርስዋን ስጡት።


ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ አስገባቸው።


ንጉሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፥ ነገር ግን የበኵር ልጁ ነበረና ስለ ወደደው የልጁን የአምኖን ነፍስ አላሳዘነም።


በእስራኤል ዘንድ ስንፍና አድርገዋልና፥ ከባልንጀሮቻቸውም ሚስቶች ጋር አመንዝረዋልና፥ ያላዘዝኋቸውንም ቃል በስሜ በሐሰት ተናግረዋልና።


የእስራኤል ማኅበር ሁሉ ቢስቱ፥ ነገሩም ከጉባኤው ፊት ቢሸሸግ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፉ፥


ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥


ከአገሩ ሕዝብም አንድ ሰው ኃጢአትን ሳያውቅ ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥራ ያለውን ትእዛዝ ቢተላለፍ፥ ቢበድልም፥


ከእነርሱም አንዳንዶቹ እንደ ሴሰኑ በአንድ ቀንም ሁለት እልፍ ከሦስት ሺህ እንደ ወደቁ አንሴስን።


ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል።


ለቅዱሳን እንደሚገባ ግን ዝሙትና ርኵሰት ሁሉ ወይም መመኘት በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤


ነገሩ ግን እውነት ቢሆን፥ በብላቴናይቱም ድንግልናዋ ባይገኝ፥


ብላቴናይቱን ወደ አባትዋ ቤት ደጅ ያውጡአት፥ በእስራኤልም ዘንድ የማይገባውን ነገር አድርጋለችና፥ በአባትዋም ቤት አመንዝራለችና የከተማዋ ሰዎች እስክትሞት ድረስ በድንጋይ ይውገሩአት፤ እንዲሁም ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።


ከእስራኤል ሴቶች ልጆች ሴት ጋለሞታ አትገኝ፥ ከእስራኤልም ወንዶች ልጆች ወንድ ጋለሞታ አይገኝ።


እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው፤


ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፥ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።


መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን፤ ሴሰኞችንና አመንዝሮችን ግን እግዚአብሔር ይፈርድባቸዋል።


ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።


እርም የሆነውም ነገር የተገኘበት ሰው የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን አፍርሶአልና፥ በእስራኤልም ዘንድ በደል አድርጎአልና እርሱና ያለው ሁሉ በእሳት ይቃጠላሉ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


እኔም ቁባቴን ይዤ ቈራረጥኋት፥ በእስራኤልም ዘንድ እንደዚህ ያለ ኃጢአትና ስንፍና ስለ ተሠራ ወደ እስራኤል ርስት አገር ሁሉ ሰደድሁ።


跟着我们:

广告


广告