Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 34:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ያዕቆብ፣ ልጁን ዲናን ሴኬም እንዳስነወራት ሰማ፤ በዚህ ጊዜ ወንዶች ልጆቹ ከብቶቹን በመስክ ያግዱ ነበር፤ ያዕቆብም ልጆቹ እስኪመለሱ ድረስ ታግሦ ቈየ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ያዕቆብም ልጁን ዲናን እንዳስነወራት ሰማ፥ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በመስክ ተሰማርተው ነበር፥ ያዕቆብም እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ያዕቆብ ልጁ ዲና ክብረ ንጽሕናዋ እንደ ተደፈረ ሰማ፤ ነገር ግን ወንዶች ልጆቹ የከብት መንጋ ይዘው ተሰማርተው ስለ ነበር፥ እነርሱ እስከሚመጡ ዝም ብሎ ቈየ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ያዕ​ቆ​ብም ልጁን ዲናን የኤ​ሞር ልጅ እን​ዳ​ስ​ነ​ወ​ራት ሰማ፤ ልጆ​ቹም ከከ​ብ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር በም​ድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕ​ቆ​ብም ልጆቹ እስ​ኪ​መጡ ድረስ ዝም አለ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 34:5
13 交叉引用  

በዚያም ቀን ከተባቶቹ ፍየሎች ሽመልመሌ መሳይና ነቍጣ ያለባቸውን፥ ከእንስቶቹም ፍየሎች ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸውን ነጭ ያለበትን ማንኛውንም ሁሉ ከበጎቹም መካከል ጥኩሩን በግ ሁሉ ለይቶ ለልጆቹ ሰጣቸው።


ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፦ ይህችን ብላቴና አጋባኝ ብሎ ነገረው።


የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ ወጣ።


ትቀመጡ እንዲህ በሉት፦ እኛ ባሪያዎችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስለ አሁን ድረስ እኝም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን።


አቤሴሎምም እኅቱን ትዕማርን ስላሳፈራት አምኖንን ጠልቶታልና አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካምም አልተናገረውም።


ሙሴም አሮንን፦ እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ፥ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው አለው፤ አሮንም ዝም አለ።


ታላቁ ልጁ በእርሻ ነበረ፤ መጥቶም ወደ ቤት በቀረበ ጊዜ የመሰንቆና የዘፈን ድምፅ ሰማ፤


እርሱ ግን መልሶ አባቱን፦ እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት እንደ ባሪያ ተገዝቼልሃለሁ ከትእዛዝህም ከቶ አልተላለፍሁም፤ ለእኔም ከወዳጆቼ ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ ጥቦት ስንኳ አልሰጠኸኝም፤


ምናምንቴዎች ሰዎች ግን፦ ይህ ሰው እንዴት ያድነናል? ብለው ናቁት፥ እጅ መንሻም አላመጡለትም።


ሳሙኤልም እሴይን፦ የቀረ ሌላ ልጅ አለህን? አለው። እርሱም፦ ታናሹ ገና ቀርቶአል፥ እነሆም፥ በጎችን ይጠብቃል አለ። ሳሙኤልም እሴይን፦ እርሱ እስኪመጣ ድረስ አንረፍቅምና ልከህ አስመጣው አለው።


ዳዊትም የአባቱን በጎች ለመጠበቅ ከሳኦል ዘንድ ወደ ቤተ ልሔም ይመላለስ ነበር።


跟着我们:

广告


广告