Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 34:30 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ እኔ በቁጥር ጥቂት ነኝ እነርሱ በእኔ ላይ ይስበሰቡና ይመቱኛል እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ያዕቆብም ስምዖንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በዚህ አገር በሚኖሩት በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ዘንድ እንደ ጥንብ አስቈጠራችሁኝ፤ ጭንቀትም እንዲደርስብኝ አድርጋችኋል። እኛ በቍጥር አነስተኞች ነን፤ ተባብረው ቢነሡብኝና ቢያጠቁኝ እኔና ቤተ ሰቤ መጥፋታችን አይደለምን?”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ያዕቆብም ሌዊንና ስሞዖንን እንዲህ አለ፦ “በዚች አገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዛውያን ሰዎች የተጠላሁ ታደርጉኝ ዘንድ እኔን አስጨነቃችሁኝ፥ እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፥ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይመቱኛል፥ እኔም ከወገኔ ጋር እጠፋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ያዕቆብ ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፤ “በእኔ ላይ ከባድ ችግር አመጣችሁብኝ፤ እነሆ በዚህ ድርጊት የተነሣ በዚህች ምድር የሚኖሩ ከነዓናውያንና ፈሪዛውያን ይጠሉኛል፤ እኛ በቊጥር አነስተኞች ነን፤ እነርሱ ተባብረው ቢያጠቁን እኔና ቤተሰቤ እንጠፋለን።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ያዕ​ቆ​ብም ስም​ዖ​ን​ንና ሌዊን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ክፉ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብኝ፤ በዚች ሀገር በሚ​ኖሩ በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን ሰዎች ዘንድ አስ​ጠ​ላ​ች​ሁኝ። እኔ በቍ​ጥር ጥቂት ነኝ፤ እነ​ርሱ በእኔ ላይ ይሰ​በ​ሰ​ቡና ይወ​ጉ​ኛል፤ እኔና ቤቴም እን​ጠ​ፋ​ለን።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 34:30
33 交叉引用  

የግብፅ ሰዎች ያዩሽ እንደ ሆነ፥ ሚስቱ ናት ይላሉ እኔንም ይገድሉኛል፥ አንቺንም በሕይወት ይተዉሻል።


ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤


አብራምም እስከ ሴኬም ስፍራ እስከ ሞሬ የአድባር ዛፍ ድረስ በምድር አለፈ፤ የከነዓን ሰዎችም በዚያን ጊዜ በምድሩ ነበሩ።


የአብራምንና የሎጥን መንጎች በሚጠብቁት መካከልም ጠብ ሆነ፤ በዚያም ዘመን ከነዓናውያንና ፌርዛውያን በዚያች ምድር ተቀምጠው ነበር።


የአገሩ አለቃ የኤዊያዊ ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት ወሰዳርም ከእርስዋም ጋር ተኛ አስነወራትም።


ሀብታቸውን ሁሉ ሕፃናቶቻቸውንና ሴቶቻቸውንም፥ ሁሉ ማረኩ በቤት ያለውንም ሁሉ ዘረፉ።


እነርሱም፦ በጋለሞታ እንደሚደረግ በእኅታችን ያደርግባትን? አሉ።


ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብፅ የገቡት ሰዎች ሁሉ ከጉልበቱ የወጡት ከልጆቹ ሚስቶች ሌላ ሁላቸው ስድሳ ስድስት ናቸው።


በግብፅ ምድር የተወለዳለት የዮሴፍም ልጆች ሁለት ናቸኤ ወደ ግብፅ የገቡት የያዕቆብ ቤተስዎች ሁሉ ሰባ ናቸው።


የአሞን ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደተጠሉ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከሶርያውያን ከቤትሮዖብና ከሱባ ሀያ ሺህ እግረኞች፥ ከመዓካ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎች፥ ከጦብም አሥራ ሁለት ሺህ ሰዎች ቀጠሩ።


አኪጦፌልም አቤሴሎምን፦ ቤት ሊጠብቁ ወደ ተዋቸው ወደ አባትህ ቁባቶች ግባ፥ እስራኤልም ሁሉ አባትህን እንዳሳፈረኸው ይሰማሉ፥ ከአንተም ጋር ያሉት ሁሉ እጃቸው ይበረታል አለው።


ሃዳድም ካደረገው ክፋት ሌላ በሰሎሞን ዘመን ሁሉ የእስራኤል ጠላት ነበረ።


ኤልያስም “እስራኤልን የምትገለባብጡ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትታችሁ በኣሊምን የተከተላችሁ፥ አንተና የአባትህ ቤት ናችሁ እንጂ እኔ አይደለሁም።


ባሪያዎቹ የእስራኤል ዘር፥ ለእርሱም የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች ሆይ! የሠራትን ድንቅ፥ ተአምራቱንና የአፉን ፍርድ አስቡ።


ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ እጅግ ጥቂቶችና ስደተኞች ሲሆኑ ነው።


የአሞንም ልጆች በዳዊት ዘንድ እንደ ተጠሉ ባዩ ጊዜ ሐኖንና የአሞን ልጆች ከመስጴጦምያ፥ ከአራምመዓካ፥ ከሱባ ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ይቀጥሩ ዘንድ አንድ ሺህ መክሊት ብር ላኩ።


የከርሚም ልጅ እስራኤልን ያስጨነቀ፥ እርሙንም ሰርቆ የበደለ አካን ነበረ።


እነርሱም፦ “በፈርዖንና በባሪያዎቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድሉንም ዘንድ ሰይፍን በእጃቸው ሰጥታችኋቸዋልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም፤” አሉአቸው።


በምድር ላይ ያለውን የእንስሳን ሁሉ ምሳሌ፥ በሰማይም በታች የሚበርረውን የወፍን ሁሉ ምሳሌ፥


እግዚአብሔርም በአሕዛብ መካከል ይበትናችኋል፥ እግዚአብሔር በውስጣቸው በሚያኖራችሁ በአሕዛብ መካከልም ጥቂቶች ሆናችሁ ትቀራላችሁ።


እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ስለ በዛችሁ አይደለም፤ እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ጥቂቶች ነበራችሁና፤


ኢያሱም፦ ለምን አስጨነቅኸን? እግዚአብሔር ዛሬ ያስጨንቅሃል አለው፥ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፥ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።


እስራኤልም ሁሉ ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግሞም እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ዘንድ እንደ ተጸየፉ ሰሙ፥ ሕዝቡም ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ።


ሳሙኤልም፦ እንዴት እሄዳለሁ? ሳኦል ቢሰማ ይገድለኛል አለ። እግዚአብሔርም፦ አንዲት ጊደር ይዘህ ሂድና፦ ለእግዚአብሔር እሠዋ ዘንድ መጣሁ በል።


ዳዊትም በልቡ፦ አንድ ቀን በሳኦል እጅ እጠፋለሁ ወደ ፍልስጥኤማውያንም ምድር ከመሸሽ በቀር የሚሻለኝ የለም፥ ሳኦልም በእስራኤል አውራጃ ሁሉ እኔን መሻት ይተዋል፥ እንዲህም ከእጁ እድናለሁ አለ።


አንኩስም፦ በሕዝቡ በእስራኤል ዘንድ እጅግ የተጠላ ሆኖአል፥ ሰለዚህም ለዘላለም ባሪያ ይሆነኛል ብሎ ዳዊትን አመነው።


跟着我们:

广告


广告