Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 34:20 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ኤሞርና ሴኬም ልጁም ወደ ከተማቸው አደባባይ ገቡ ለከተማቸውም ሰዎች እንዲህ ብለው

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ስለዚህ ኤሞርና ልጁ ሴኬም ይህንኑ ለወገኖቻቸው ለመንገር ወደ ከተማቸው በር ሄዱ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ኤሞርና ሴኬም ልጁም ወደ ከተማቸው አደባባይ ገቡ፥ ለከተማቸውም ሰዎች እንዲህ ብለው ነገሩ፦

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ስለዚህ ሐሞርና ልጁ ሴኬም በከተማው በር አጠገብ ወዳለው መሰብሰቢያ ቦታ ሄዱ፤ ለከተማይቱ ነዋሪዎች እንዲህ በማለት ንግግር አደረጉ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ኤሞ​ርና ልጁ ሴኬ​ምም ሄዱና ወደ ከተ​ማ​ቸው በር ደረሱ፤ ለከ​ተ​ማ​ቸ​ውም ሰዎች ሁሉ እን​ዲህ ብለው ነገሩ፦

参见章节 复制




ዘፍጥረት 34:20
14 交叉引用  

በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፦ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር እንዳል አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤


ኤፍሮን፥ በኬጢ ሰው ኤፍሮን፥ የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ


ብላቴናውም ያሉትን ያደርግ ዘንድ አልዘገየም የያዕቆብን ልጅ ወደዶአልና እርሱም በአባቱ ቤት ካሉት ሁሉ የከበረ ነበረ።


ነገሩ፦ እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው በምድራችን ይቀመጡ ይነግዱባትም እነሆም ምድሪቱ ሰፊ ናት ሴቶች ልጆቻቸውን እንውሰድ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻቸንን እንስጥ


አቤሴሎምም በማለዳ ተነሥቶ በበሩ አደበባይ ይቆም ነበር፥ አቤሴሎምም ከንጉሥ ለማስፈረድ ጉዳይ የነበረውን ሁሉ ወደ እርሱ እየጠራ፦ አንተ ከወዴት ከተማ ነህ? ብሎ ይጠይቅ ነበር። እርሱም፦ እኔ ባሪያህ ከእስራኤል ነገድ ከአንዲቱ ነኝ ብሎ ይመልስ ነበር።


ወደ ከተማይቱ በር በወጣሁ ጊዜ፥ በአደባባዩም ወንበሬን ባኖርሁ ጊዜ፥


በበሩ አደባባይ የሚገሥጸውን ጠሉ፥ እውነትም የሚናገረውን ተጸየፉ።


ጻድቁን የምታስጨንቁ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችጋረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ፥ በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።


ክፉውን ጥሉ፥ መልካሙንም ውደዱ፥ በበሩም አደባባይ ፍርድን አጽኑ፥ ምናልባት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ለዮሴፍ ቅሬታ ይራራ ይሆናል።


የምትሠሩት ነገር ይህ ነው፥ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ፥ በበር አደባባያችሁም የእውነትንና የሰላምን ፍርድ ፍረዱ፥


ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ።


ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ “አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ፤” አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።


跟着我们:

广告


广告