Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 33:17 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ በዚያም ለእርሱ ቤትን ሠራ ለከብቶች ዳሶችን አደረገ፤ ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም ሱኮት ብሎ ጠራው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ፤ እዚያም ለራሱ መጠለያ፣ ለከብቶቹም በረት ሠራ፤ ከዚህም የተነሣ የቦታው ስም ሱኮት ተባለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ያዕቆብ ግን ወደ “ሱኮት” ሄደ፥ ከዚያም ለራሱ ቤትን ሠራ፥ ለከብቶቹም ዳሶችን አደረገ። ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም “ሱኮት” ብሎ ጠራው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 ያዕቆብ ግን ወደ ሱኮት አመራ፤ እዚያም ለራሱ ቤትና ለከብቶቹም መጠለያ ሠራ፤ ስለዚህ ያ ስፍራ ሱኮት ተባለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ያዕ​ቆብ ግን በሰ​ፈሩ አደረ፤ በዚ​ያም ለእ​ርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከ​ብ​ቶ​ቹም ዳሶ​ችን አደ​ረገ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም ማኅ​ደር ብሎ ጠራው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 33:17
10 交叉引用  

ዔሳውም በዚያን ቀን ወደ ሴይር መንገዱን ተመለሰ።


በዮርዳኖስ ሜዳ በሱኮትና በጸርታን መካከል ባለው በወፍራሙ መሬት ውስጥ አስፈሰሰው።


የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተነሥተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከሕፃናቱም ሌላ ስድስት መቶ ሺህ ሰው የሚያህል እግረኛ ነበረ።


ከሱኮትም ተጓዙ፤ በምድረ በዳውም ዳር በኤታም ሰፈሩ።


በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትኒምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኪኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበር።


ከሱኮትም ሰዎች አንድ ብላቴና ይዞ ጠየቀው፥ እርሱም የሱኮትን አለቆችና ሽማግሌዎች ሰባ ሰባት ሰዎች ጻፈለት።


የከተማይቱንም ሽማግሌዎች ያዘ፥ የምድረ በዳንም እሾህና ኵርንችት ወስዶ የሱኮትን ሰዎች ገረፋቸው።


የሱኮትንም ሰዎች፦ የምድያምን ነገሥታት ዛብሄልንና ስልማናን ሳሳድድ፥ ደክመዋልና እኔን ለተከተሉ ሕዝብ እንጀራ፥ እባካችሁ፥ ስጡ አላቸው።


ከዚያም ወደ ጵኒኤል ወጣ፥ ለጵኒኤልም ሰዎች እንዲሁ አላቸው፥ የጵንኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለሱለት።


跟着我们:

广告


广告