Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 33:11 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ይህችንም ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል እግዚአብሔር በቸርነት ስጥቶኛልና ለእኔም ብዙ አለኝና። እስኪቀበለውም ድረስ ዘበዘበው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር በቸርነቱ አሟልቶ ስለ ሰጠኝ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝና ያቀረብሁልህን ስጦታዬን እባክህ ተቀበለኝ” አለው። ያዕቆብ አጥብቆ ስለ ለመነው፣ ዔሳው እጅ መንሻውን ተቀበለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ይህንም ያመጣሁልህን ስጦታዬን ተቀበል፥ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ጎብኝቶኛልና፥ ለእኔም በቂ አለኝና።” በዚህም መልክ ግድ አለው፥ እርሱም ተቀበለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ስለዚህ እባክህ ይህን ያቀረብኩልህን ስጦታ ተቀበለኝ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ሰጥቶኛል” አለ። ስጦታውን እንዲቀበለው ያዕቆብ ዔሳውን አጥብቆ ለመነው። እርሱም ተቀበለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 33:11
21 交叉引用  

ያ ሰውም እጅግ ባለ ጠጋ ሁነ፤ ብዙም ከብት ሴቶችም ወንዶችም ባሪያዎች ግመሎችም አህዮችም ሆኑለት።


እጅ መንሻው ከእርሱ ቀድሞ አለፈ እርሱ ግን በዚያች ሌሊት በሰፈር አደረ።


ያዕቆብም አለ፦ እንደዚህ አይደለም ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።


እርሱም፦ ተነሣና እንሂድ እኔም በፊትህ እሄዳለሁ አለ።


ዔሳውም፦ ለእኔ ብዙ አለኝ ወንድሜ ሆይ የአንተ ለአንተ ይሁን አለ።


እስኪያፍርም ድረስ ግድ ባሉት ጊዜ “ስደዱ” አለ፤ አምሳም ሰዎች ሰደዱ፤ ሦስት ቀንም ፈልገው አላገኙትም።


ንዕማንም “ሁለት መክሊት ትወስድ ዘንድ ይፈቀድልህ፤” አለ፤ ግድ አለውም፤ ሁለቱንም መክሊት ብር በሁለት ከረጢት ውስጥ አሰረና ከሁለት መለወጫ ልብስ ጋር ለሁለት ሎሌዎቹ አስያዘ፤ እነርሱም ተሸክመው በፊቱ ሄዱ።


ጌታውም ባሪያውን፦ ቤቴ እንዲሞላ ወደ መንገድና ወደ ቅጥር ውጣና ይገቡ ዘንድ ግድ በላቸው፤


ስለዚህም ማንም በሰው አይመካ። ነገር ሁሉ የእናንተ ነውና፤


ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።


ነገር ግን ሁሉ አለኝ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ ተሞልቼአለሁ።


ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።


ካሌብም፦ ምን ፈለግሽ? አላት። እርስዋም፦ በረከትን ስጠኝ፥ በደቡብም በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና አሁን ደግሞ የውኃውን ምንጭ ስጠኝ አለችው። እርሱም የላይኛውንና የታችኛውን ምንጭ ሰጣት።


እርስዋም፦ በረከትን ስጠኝ፥ በደቡብ በኩል ያለውን ምድር ሰጥተኸኛልና የውኃ ምንጭ ደግሞ ስጠኝ አለችው። ካሌብም ላይኛውንና ታችኛውን ምንጭ ሰጣት።


አሁንም ባሪያህ ወደ ጌታዬ ያመጣችው ይህ መተያያ ጌታዬን ለሚከተሉ ጕልማሶች ይሰጥ።


ዳዊትም ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ ለዘመዶቹ ለይሁዳ ሽማግሌዎች፦ እነሆ፥ ከእግዚአብሔር ጠላቶች ምርኮ በረከትን ተቀበሉ ብሎ ከምርኮው ሰደደላቸው።


跟着我们:

广告


广告