Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 33:10 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ያዕቆብም አለ፦ እንደዚህ አይደለም ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ያዕቆብም፣ “የለም፣ እንዲህ አይደለም፤ በአንተ ዘንድ ሞገስ አግኝቼ እንደ ሆነ፣ እጅ መንሻዬን ተቀበል፤ በመልካም ሁኔታ ተቀብለኸኝ ፊትህን ማየት መቻሌን የእግዚአብሔርን ፊት እንደ ማየት እቈጥረዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ያዕቆብም አለ፥ “እንደዚህ አይሁን፥ ነገር ግን በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደሆንሁ፥ እጅ መንሻዬን ተቀበለኝ፥ የእግዚአብሔርን ፊት እንደሚያይ ፊትህን አይቼአለሁና፥ በቸርነትም ተቀብለኸኛልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ያዕቆብ ግን “እንዲህስ አይሁን፤ በእርግጥ የምትወደኝ ከሆነ እባክህ ስጦታዬን ተቀበል፤ ፍቅር ስላሳየኸኝ፥ የአንተን ፊት ማየት የእግዚአብሔርን ፊት እንደማየት ያኽል እቈጥረዋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መን​ሻ​ዬን ከእጄ ተቀ​በ​ለኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት እን​ደ​ሚ​ያይ ፊት​ህን አይ​ቻ​ለ​ሁና፥ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​ብ​ለ​ኸ​ኛ​ልና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 33:10
19 交叉引用  

እነሆ ባሪያህ በፊትህ ሞገስን አግኝቶአል ነፍሴን ለማዳን ያደረግህልኝን ምሕረትህንም አብዝተሃል ክፋ እንዳያጋኘኝና እንዳልሞት ወደ ተራራ ሸሽቼ አመልጥ ዘንድ አልችልም


ያዕቆብም፦ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ዽኒኤል ብሎ ጠራው።


ይህችንም ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል እግዚአብሔር በቸርነት ስጥቶኛልና ለእኔም ብዙ አለኝና። እስኪቀበለውም ድረስ ዘበዘበው።


ዔሳውም፦ ለእኔ ብዙ አለኝ ወንድሜ ሆይ የአንተ ለአንተ ይሁን አለ።


ይሁዳም እንዲህ አለው፦ ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዪም ብሎ በብርቱ ቃል አስጠነቀቀን።


የእስራኤልም የሞቱ ቀን ቀረበ ልጁን ዮሴፍንም ጠርቶ እንዲህ አለው፦ በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ እጅህን ከጭኔ በታች አድርግ በግብፅ ምድርም እንዳትቀብርኝም ምሕረትና እውነትን አድርግልኝ


የልቅሶውም ወራት ባለፈ ጊዜ ዮሴፍ ለፈርዓን ቤተ ሰቦች እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ እኔ በፊታችሁ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦


ንጉሡም፦ ወደ ቤቱ ይሂድ እንጂ ፊቴን እንዳያይ አለ፥ አቤሴሎምም ወደ ቤቱ ሄደ፥ የንጉሡንም ፊት አላየም።


አቤሴሎምም በኢየሩሳሌም ሁለት ዓመት ሙሉ የንጉሡን ፊት ሳያይ ተቀመጠ።


አቤሴሎምም ኢዮአብን መልሶ፦ ከጌሹር ለምን መጣሁ? በዚያም ተቀምጩ ብሆን ይሻለኝ ነበር ብለህ እንድትነግረው ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ጠራሁህ፥ አሁንም የንጉሡን ፊት ልይ፥ ኃጢአት ቢሆንብኝ ይግደለኝ አለው።


ዳዊትም፦ ይሁን፥ ከአንተ ጋር ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፥ ነገር ግን አንድ ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ፊቴን ለማየት በመጣህ ጊዜ፥ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ካላመጣህልኝ ፊቴን አታይም አለ።


ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እርሱም ሞገስን ይሰጠዋል፥ ፊቱንም በደስታ ያሳየዋል፥ ለሰውም ጽድቁን ይመልስለታል።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እስራኤል ማረፊያ ሊሻ በሄደ ጊዜ ከሰይፍ የተረፈው ሕዝብ በምድረ በዳ ሞገስ አገኘ።


ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን እንዳትንቁ ተጠንቀቁ፤ መላእክቶቻቸው በሰማያት ዘወትር በሰማያት ያለውን የአባቴን ፊት ያያሉ እላችኋለሁና።


ስሙም በግምባሮቻቸው ይሆናል።


በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት “እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን?” አለችው።


ዳዊትም፦ እኔ በፊትህ ሞገስ እንዳገኘሁ አባትህ በእውነት ያውቃል፥ እርሱም፦ ዮናታን እንዳይከፋው አይወቅ ይላል፥ ነገር ግን ሕያው እግዚአብሔርን! በሕያው ነፍስህም እምላለሁ! በእኔና በሞት መካከል አንድ እርምጃ ያህል ቀርቶአል ብሎ ማለ።


跟着我们:

广告


广告