Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 32:31 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ዽኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ጵኒኤልንም እንዳለፈ ፀሓይ ወጣችበት፤ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ጵኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ያዕቆብ ከጵንኤል ተነሥቶ ሲሄድ ፀሐይ ወጥታ ነበር፤ በጭኑም ሕመም ምክንያት ያነክስ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በተወ ጊዜ ፀሐይ ወጣ​ች​በት። እር​ሱም በጭኑ ምክ​ን​ያት ያነ​ክስ ነበር።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 32:31
19 交叉引用  

እርስዋም ይናገራት የነበረውን የእግዚአብሔርን ስም ኤልሮኢ ብላ ጠራች የሚያየኝን በውኑ እዚህ ደግሞ አየሁትን? ብላለችና።


ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ ተነሣ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውስድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፉ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር።


ሎጥ ወደ ዞዓር በገብ ጊዜ ፀሐይ በምድር ላይ ወጣች።


እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ።


ስለዚህም የእስራኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወርችን ሹልዳ አይበሉም፤ የያዕቆብን ጭን ይዞ የወርችን ሹልዳ አደንዝዞአልን።


ኢዮርብዓምም በተራራማው በኤፍሬም አገር ሴኬምን ሠርቶ በዚያ ተቀመጠ፤ ደግሞም ከዚያ ወጥቶ ጵኒኤልን ሠራ።


ወይፈኑንም ወስደው አዘጋጁ፤ ከጥዋትም እስከ ቀትር ድረስ “በኣል ሆይ! ስማን፤” እያሉ የበኣልን ስም ጠሩ። ድምፅም አልነበረም፤ የሚመልስም አልነበረም፤ በሠሩትም መሠዊያ ዙሪያ እያነከሱ ያሸበሽቡ ነበር።


የእስራኤልንም አምላክ አዩ፤ ከእግሩም በታች እንደ ሰማይ መልክ የሚያበራ እንደ ብሩህ ሰንፔር ድንጋይ የሚመስል ወለል ነበረ።


እጁንም በእስራኤል አዛውንቶች ላይ አልዘረጋም፤ እነርሱም እግዚአብሔርን አዩ፥ በሉም ጠጡም።


እኔም፦ ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን ስላዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ።


ነገር ግን ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፥ እናንተም ትወጣላችሁ፥ እንደ ሰባም እምቦሳ ትፈነጫላችሁ።


ስለዚህም በመገለጥ ታላቅነት እንዳልታበይ የሥጋዬ መውጊያ፥ እርሱም የሚጎስመኝ የሰይጣን መልእክተኛ ተሰጠኝ፤ ይኸውም እንዳልታበይ ነው።


እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።


አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር ሰውዬውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል።


ከሥጋ ለባሽ ሁሉ እኛ እንደ ሰማን በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን ነው?


ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ አየ፥ ጌዴዎንም፦ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ ወዮልኝ፥ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና አለ።


እግዚአብሔርም፦ ሰላም ለአንተ ይሁን፥ አትፍራ፥ አትሞትም አለው።


ከዚያም ወደ ጵኒኤል ወጣ፥ ለጵኒኤልም ሰዎች እንዲሁ አላቸው፥ የጵንኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለሱለት።


跟着我们:

广告


广告