ዘፍጥረት 32:30 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ያዕቆብም፦ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ ሰውነቴም ድና ቀረች ሲል የዚያን ቦታ ስም ዽኒኤል ብሎ ጠራው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ስለዚህ ያዕቆብ፣ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እንኳ ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል፣ የዚያን ቦታ ስም ጵኒኤል አለው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ስለዚህ ያዕቆብ፦ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፥ ሆኖም ሕይወቴ ተርፋለች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ጵኒኤል” ብሎ ጠራው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው። 参见章节 |