Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 32:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ያዕቆብም ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም አገር ከፊቱ መልእክተኞችን ላከ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ያዕቆብም በኤዶም አገር ሴይር በተባለው ምድር ወደሚኖረው ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞችን አስቀድሞ ላከ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም አገር ከፊቱ መልእክተኞችን ላከ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከዚህ በኋላ ያዕቆብ በኤዶም አገር ሤዒር ተብላ በምትጠራው ምድር ወደሚኖረው ወደ ወንድሙ ወደ ዔሳው መልእክተኞች አስቀድሞ ላከ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 32:3
23 交叉引用  

የሖር ሰዎችንም በሴይር ተራራቸው በበረሀ አጠገብ እስካለች እስከ ኤል ፋራን ድረስ መቱ።


ዔሳውም ያዕቆብን፦ ከዚህ ከቀዩ ወጥ አብላኝ እኔ እጅግ ደክሜአለሁና አለው ስለዚህ ስሙ ኤዶም ተባለ።


ከወንድሜ ከዔሳው እጅ አድነኝ፤ መጥቶ እንዳያጠፋኝ እናቶችንም ከልጆች ጋር እንዳያጠፋ እኔ እፈራዋለሁና።


ያዕቆብም እጅግ ፈርቶ ተጨነቀ ከእርሱም ጋር ያሉትን ሰዎች መንጎችንም ላሞችንም ግመሎችንም በሁለት ወገን ከፈላቸው እንዲህም አለ፦


ጌታዬ ከባሪያው ፊት ቀድሞ ይለፍ እኔም ወደ ሴይር ከጌታዬ ዘንድ እስክደርስ ድረስ ከፊቴ ባሉት በእንስሳቱ እርምጃና በሕፃናቱ እርምጃ መጠን በዝግታ እከተላለሁ።


ዔሳውም በዚያን ቀን ወደ ሴይር መንገዱን ተመለሰ።


የሳኦልም ጭፍራ አለቃ የኔር ልጅ አበኔር የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፥


ኤልሳዕም “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይኖቹን እባክህ ግለጥ፤” ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፤ አየም፤ እነሆም፥ በኤልሳዕ ዙሪያ ያሉት የእሳት ፈረሶችና ሠረገሎች ተራራውን ሞልተውት ነበር።


እንደ እግዚአብሔርም ቃል የሳኦልን መንግሥት ወደ እርሱ ይመልሱ ዘንድ በኬብሮን ሳለ ወደ ዳዊት የመጡት የሠራዊቱ አለቆች ቍጥር ይህ ነው።


አንቺ ሱላማጢስ ሆይ፥ ተመለሽ፥ ተመለሽ፥ እናይሽ ዘንድ ተመለሽ፥ ተመለሽ። በሱላማጢስ ምን ታያላችሁ? እርስዋ እንደ መሃናይም ዘፈን ናት።


ስለ ኤዶሚያስ የተነገረ ሸክም። አንዱ ከሴይር፦ ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ጕበኛ ሆይ፥ ሌሊቱ ምን ያህል ነው? ብሎ ጠራኝ።


ስለ ኤዶምያስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን?


እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፥ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፥ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።


ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል።


በፊቱም መልክተኞችን ሰደደ። ሄደውም ሊያሰናዱለት ወደ አንድ ወደ ሳምራውያን መንደር ገቡ፤


በሴይር ተራራ መንገድ ከኮሬብ እስከ ቃዴስ በርኔ ድረስ የአሥራ አንድ ቀን መንገድ ነው።


ሖራውያንን ከፊታቸው አጥፍቶ በሴይር ለተቀመጡት ለዔሳው ልጆች እንዳደረገ እንዲሁ ለእነርሱ አደረገ፤ እነርሱንም አሳድደው በስፍራቸው እስከ ዛሬ ድረስ ተቀመጡ።


የሴይርን ተራራ ለዔሳው ርስት አድርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከምድራቸው የጫማ መርገጫ ታህል እንኳ አልሰጣችሁምና አትጣሉአቸው።


ድንበራቸውም ከመሃናይም ጀምሮ የባሳን ንጉሥ የዐግ መንግሥት፥ ባሳን ሁሉ፥ በባሳንም ያሉት የኢያዕር መንደሮች ሁሉ ስድሳው ከተሞች፥ የገለዓድም እኩሌታ፥


ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፥ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፥ ያዕቆብም ልጆቹም ወደ ግብፅ ወረዱ።


跟着我们:

广告


广告