Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 31:5 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 እንዲህም አላቸው፦ የአባታችሁ ፊት ከእኔ ጋር እንደ ዱሮ እንዳልሆን አያለሁ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ ስለ እኔ ያለው አመለካከት እንደ ቀድሞው አለመሆኑን ተረድቻለሁ፤ ቢሆንም የአባቴ አምላክ አልተለየኝም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንዲህም አላቸው፥ “አባታችሁ ከእኔ ጋር እንደ ቀድሞው እንደማይወደኝ አያለሁ፥ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንዲህም አላቸው፤ “አባታችሁ እንደ ቀድሞው ጊዜ እንደማይወደኝ ተረድቼአለሁ፤ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር አለ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ የአ​ባ​ታ​ችሁ ፊት እንደ ዱሮ ከእኔ ጋር እን​ዳ​ል​ሆነ አያ​ለሁ፤ ነገር ግን የአ​ባቴ አም​ላክ ከእኔ ጋር ነው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 31:5
15 交叉引用  

በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፤ በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤


በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና እባርክሃለሁ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።


እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር እንዲህም አለ፦ የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤


እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምትሄድባትም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድርስ አልተውህምና።


ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።


ክፉ አደርግባችሁ ዘንድ ኃይል ነበረኝ፤ ነገር ግን የአባታችሁ አምላክ ትናንት፦ ያዕቆብን በክፉ ነገር እንዳትናገረው ተጠንቀቅ ብሎ ነገረኝ።


ያዕቆብም ልኮ ራሔልንና ልያን ወደ በጎቹ ስፍራ ወደ ሜዳ ጠራቸው፥


የአባቴ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሃት ከእኔ ጋር ባይሆንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር እግዚአብሔር መከራዬንና የእጆቼን ድካም አየ፥ ትናንትም ገሠጸህ።


የአብርሃም አምላክ የናኮርም አምላክ የአባታቸውም አምላክ በእኛ መካከል ይፍረድ። ያዕቆብ በአባቱ በይስሐቅ ፍርሃት ማለ።


ያዕቆብም አለ፦ የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፦ ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ


ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከው እንዲህም አለ፦ አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ ዛሬ ድርስ እኔን የመገባኝ እግዚአብሔር ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር ከክፋ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እርሱ


ዮሴፍን እንዲህ በሉት፦ እባክህ የውንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና አሁን እባክህ የአባትህ አምላክ ባሪያዎች የበደሉን ይቅር በል።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፥ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤


跟着我们:

广告


广告