Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 31:34 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 ራሔልም ተራፊምን ወሰዳ ከግመል ኮርቻ በታች ሸሸገች በላዩም ተቀመጠችበት። ላባም ድንኳኑን ሁሉ ፈለገ አንዳችም አላገኘም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ራሔል የጣዖታቱን ምስል ከግመሏ ኮርቻ ሥር ሸሽጋ፣ በላዩ ተቀምጣበት ነበር፤ ላባም ድንኳኑን አንድ በአንድ በርብሮ ምንም ሊያገኝ አልቻለም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 ራሔልም ተራፊምን ወስዳ ከግመል ኮርቻ በታች ሸሸገች፥ በላዩም ተቀመጠችበት። ላባም ድንኳኑን ሁሉ ፈለገ፥ አንዳችም አላገኘም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ራሔል ግን ጣዖቶቹን ወስዳ በግመሉ ኮርቻ ሥር በመሰወር በላያቸው ላይ ተቀምጣባቸው ነበር፤ ላባ በድንኳኑ ውስጥ ያለውን ጓዝ ሁሉ በርብሮ ምንም ነገር አላገኘም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ወስዳ ከግ​መል ኮርቻ በታች ሸሸ​ገች፤ በላ​ዩም ተቀ​መ​ጠ​ች​በት። ላባም ድን​ኳ​ኑን ሁሉ ፈለገ፤ አን​ዳ​ችም አላ​ገ​ኘም።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 31:34
8 交叉引用  

ያዕቆብም ተነሣ ልጆቹንና ሚስቶቹንም በግመሎች ላይ አስቀመጠ፤


ላባ ግን በጎቹን ለመሸለት ሄዶ ነበር ራሔልም የአባትዋን ተራፌም ሰረቀም።


ላባም ወደ ያዕቆብ ድንኳንና ወደ ልያ ድንኳን ወደ ሁለቱም ባሪይዎች ድንኳን ገባ ነገር ግን አላገኘም።


እርስዋም አባትዋን፦ በፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፤ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና አለችው። እርሱም ፈለገ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም።


የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ዓምድ፥ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፥


ፈሳሽ ነገር ያለበት ሰው የተቀመጠበት ኮርቻ ሁሉ ርኩስ ነው።


እርሱም፦ የሠራኋቸውን አማልክቴን ካህኑንም ይዛችሁ ሄዳችኋል፥ ሌላ ምን አለኝ? እናንተስ፦ ምን ሆነሃል እንዴት ትሉኛላችሁ? አለ።


ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፥ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ አለ።


跟着我们:

广告


广告