Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 31:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እግዚአብሔርም ያዕቆብን፦ ወደ አባትህ ምድር ወደ ዘመዶችህም ተመለስ ከአንተም ጋር እሆናለሁ አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔርም ያዕቆብን፣ “ወደ አባቶችህና ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ካንተ ጋራ እሆናለሁ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በዚህን ጊዜ ጌታ ያዕቆብን፥ “ወደ አባቶችህ ምድር እና ወደ ዘመዶችህ ተመለስ፥ ከአንተም ጋር እሆናለሁ” አለው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 በዚህን ጊዜ እግዚአብሔር ያዕቆብን “ወደ አባቶችህና ወደ ዘመዶችህ አገር ተመለስ፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ወደ አባ​ት​ህና ወደ ዘመ​ዶ​ችህ ሀገር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ” አለው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 31:3
26 交叉引用  

ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና።


በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፤ በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤


በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና እባርክሃለሁ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።


እነሆም፥ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት ነበር እንዲህም አለ፦ የአባትህ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ ይህችን አንተ የተኛህባትን ምድር ለአንተም ለዘርህም እሰጣለሁ፤


እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምትሄድባትም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድርስ አልተውህምና።


ያፍራህ ያብዛህ፤ ሰደተኛ ሆነህ የተቀመጥህባትን እግዚአብሔርም ለአብርሃም የሰጣትን ምድር ትወርስ ዘንድ የአብርሃም በርከት ለአንተ ይስጥህ ለዘርህም እንዲሁ እንደ አንተ።


ራሔልም ዮሴፍን ከወለደች በኋላ ያዕቆብ ላባን እንዲህ አለው፦ ወደ ስፍራዬ ወደ አገሬም እመለስ ዘንድ አሰናብተኝ።


ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።


መንጎቹንም ሁሉ የቤቱንም ዕቃ ሁሉ በሁለት ወንዞች መካከል ሳለ ያገኛቸውን ከብቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ወደ ከነዓን ምድር ሄደ።


ያዕቆብም የላባን ፊት አየ እነሆም ከእርሱ ጋር እንደ ዱሮው አልሆነም።


ያዕቆብም ልኮ ራሔልንና ልያን ወደ በጎቹ ስፍራ ወደ ሜዳ ጠራቸው፥


ለባሪያህ ከሠራኸው ከምሕረትህን ከእውነትህም ሁሉ ትንሽ ስ ስንኳ የማይገባኝ ነኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።


ላሞችንም አህዮችንም፥ በጎችን፥ ወንዶች ባሪያዎችንም ሴቶች ባሪያዎችን፥ አገኘሁ፤ አሁን፥ በፍትህ ሞገስን አገኝ ዘንድ ለጌታዬ ለማስታወቅ ላክሁ።


ያዕቆብም አለ፦ የአባቴ የአብርሃም አምላክ ሆይ፦ ወደ ምድርህ ወደ ተወለድህበትም ስፍራ ተመለስ በጎነትንም አደርግልሃለሁ ያልኸኝ እግዚአብሔር ሆይ


እግዚአብሔርም ያዕቆብን አለው፦ ተነሥተህ ወደ ቤቴል ውጣ በዚያም ኑር ከወንድምህ ከዔሳው ፊት በሸሸህ ጊዜ ለተገለጠልህ ለእግዚአብሔርም መሠውያውን አድርግ።


ተነሥተንም ወደ ቤቴል እንውጣ በዚያም በመከራዬ ጊዜ ለሰማኝ በሄድሁበትም መንገድ ከእኔ ጋር ለነበረው ለእግዚአብሔር መሠውያን አደርጋለሁ።


ዮሴፍም ወንድሞቹን አለ፦ እኔ እሞታለሁ እግዚአብሔር መጎብኘትን ይጎበኛችኍል ከዚህችም ምድር ያወጣችኍል ለአብርሃምን ለይስሕቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያደርሳችኍል።


እርሱም፦ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ምልክትህ ይህ ነው፤ ሕዝቡን ከግብፅ ባወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ ለእግዚአብሔር ትገዛላችሁ፤” አለ።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፥ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፥ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤


跟着我们:

广告


广告