ዘፍጥረት 3:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 የሁለቱም ዓይኖች ተከፈቱ፤ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ ዕራቍታቸውን መሆናቸውንም ተገነዘቡ። ስለዚህ የበለስ ቅጠል ሰፍተው አገለደሙ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፥ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ አወቁ፥ ስለዚህ የበለስን ቅጠሎች ሰፍተው በማገልደም እርቃናቸውን ሸፈኑ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 የሁለቱም ዐይኖች ተከፍተው እራቁታቸውን እንደ ሆኑ ተገነዘቡ፤ ስለዚህ የበለስ ቅጠሎችን አገናኝተው ሰፉና በማገልደም እርቃናቸውን ሸፈኑ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 የሁለቱም ዐይኖች ተከፈቱ፤ እነርሱም ዕራቁታቸውን እንደ ሆኑ ዐወቁ፤ አፈሩም፤ የበለስንም ቅጠሎች ሰፍተው ለእነርሱ ለራሳቸው ግልድም አደረጉ። 参见章节 |