Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 29:8 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 እነርሱም አሉ፦ መንጎች ሁሉ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም ከዚይም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እነርሱም፣ “መንጎቹ ሁሉ ተሰብስበው ድንጋዩ ከጕድጓዱ አፍ ካልተንከባለለ በቀር አንችልም፤ ከዚያም በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እነርሱም አሉ፦ “መንጎች ሁሉ እስኪከማቹና ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም፥ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እነርሱም “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እነ​ር​ሱም አሉ፥ “እረ​ኞች ሁሉ ካል​ተ​ሰ​በ​ሰ​ቡና ድን​ጋ​ዪ​ቱን ከጕ​ድ​ጓዱ አፍ ካላ​ነ​ሡ​አት በቀር አን​ች​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ በጎ​ቹን እና​ጠ​ጣ​ለን።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 29:8
8 交叉引用  

መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደ ገና ይገጥሙት ነበር።


እርሱም፦ ቀኑ ገና ቀትር ነው ከብቶቹ የሚከማቹበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩምአቸው አላቸው።


እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ የላባ ልጅ ራሔል ከአባትዋ በጎች ጋር ደረስች እርስዋ የአባትዋን በጎች ትጠብቅ ነበርና።


እንዲህም አሉአቸው፦ እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህንን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም ይህ ነውር ይሆንብናልና።


ለእርሱም ለብቻው አቀረቡ ለእነርሱም ለብቻቸው ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ለግብፅ ሰዎችም ለብቻቸው የግብፅ ሰዎች ከዕብራውያን ጋር መብላት አይሆንላቸውምና ይህ ለግብፅ ሰዎች እንደ መርከስ ነውና።


እርስ በርሳቸውም፦ ድንጋዩን ከመቃብር ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል? ይባባሉ ነበር፤


ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥


በከተማይቱም ዳገት በወጡ ጊዜ ቆነጃጅት ውኃውን ሊቀዱ ሲወጡ አገኙና፦ ባለ ራእይ በዚህ አለ ወይ? አሉአቸው።


跟着我们:

广告


广告