Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 28:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሁሉን ቻይ አምላክ ይባርክህ፤ ብዙ ሕዝብ እስክትሆን ድረስ ልጆች አፍራ፤ ዘርህን ያብዛው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሁሉን የሚችል አምላክም ለብዙ ሕዝብ ጉባኤ እንድትሆን ይባርክህ፥ ያፍራህ፥ ያብዛህ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ልጆችም ይስጥህ! የብዙ ሕዝቦችም አባት ያድርግህ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አም​ላኬ ከአ​ንተ ጋር ይሂድ፤ ከፍ ከፍም ያድ​ር​ግህ፤ ይባ​ር​ክህ፤ ያብ​ዛህ፤ ብዙ ሕዝ​ብም ሁን ፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 28:3
23 交叉引用  

እግዚአብሔርም ባረካቸዉ፤ እንዲህም አላቸው ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት፤ ግዙአትም የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትም ሁሉ ግዙአቸዉ።


ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቆጥር ዘንድ የሚችል ስው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቆጠራል።


ስለ እስማኤልም ሰምቼሃለሁ፤ እነሆ ባርኬዋለሁ፥ ፍሬያምም አደርገዋለሁ፥ እጅግም አበዛዋለሁ፤ አሥራ ሁለት አለቆችንም ይወልዳል፥ ታላቅ ሕዝብም እንዲሆን አደርገዋለሁ።


ርብቃንም መረቁአትና፦ አንቺ እኅታችን እልፍ አእላፋት ሁኚ፤ ዘርሽም የጠላቶችን ደጅ ይውረስ አሉአት።


በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔር ተገለጠለት፥ እንዲህም አለው፦ እኔ የአባትህ የአብርሃም አምላክ ነኝ አትፍራ፥ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና እባርክሃለሁ ስለ ባሪያዬ ስለ አብርሃም ዘርህን አበዛለሁ።


ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ ይባረላሉ፤


ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።


እግዚአብሔር አለው፦ ሁሉን ቻይ አምላክ እኔ ነኝ ብዛ ተባዛም ሕዝብና የአሕዛብ ማኅበር ከአንተ ይሆናል ነገሥታትም ከጕልበትህ ይወጣሉ።


የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው እንዲህ ሲል፦ እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ።


ሁሉን የሚችል አምላክም ሌላውን ወንድማችሁንና ብንያምን ከእናንተ ጋር ይሰድድ ዘንድ በዚያ ሰው ፊት ምሕረትን ይስጣችሁ እኔም ልጆቼን እንዳጣሁአጣሁ።


ያዕቆብ ዮሴፍን አለው፤ ሁሉን የሚችል አምላክ በከነዓን ምድር በሎዛ ተገለጠልኝ ባረከኝም እንዲህም አለኝ፦


እነሆ ፍሬያማ አደርግሃለሁ አበዛሃልሁም ለብዙም ሕዝብ ጉባኤ አደርግሃለው ይህችንም ምድር ከአንተ በኍላ ለዘላለም ርስት ለዘርህ እሰጣታለሁ።


በአባትህ በአምላክ እርሱም የሚረዳህ፥ ሁሉንም በሚችል አምላክ እርሱም የሚባርክህ፥ በሰማይ በረከት ከላይ በሚገኝ በጥልቅ በረከት ከታች በሚሠራጭ በጡትና በማኅፀን በረከት።


እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው እንዲህም አላቸው፤ ብዙ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት።


የእስራኤልም ልጆች ፍሬን አፈሩ፤ እጅግም በዙ፤ ተባዙም፤ እጅግም ጸኑ፤ ምድሪቱም በእነርሱ ሞላች።


ለአብርሃምም ለይስሐቅም ለያዕቆብም ሁሉን እንደሚችል አምላክ ተገለጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግዚአብሔር አልታወቀላቸውም ነበር።


ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክና በጉ መቅደስዋ ናቸውና መቅደስ በእርስዋ ዘንድ አላየሁም።


እነሆም፥ ቦዔዝ ከቤተ ልሔም መጣ፤ አጫጆችንም “እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፤” አላቸው። እነርሱም “እግዚአብሔር ይባርክህ፤” ብለው መለሱለት።


跟着我们:

广告


广告