Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 28:18 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ያዕቆብም በማግስቱም ማልዶ ተነሣ፣ ተንተርሶት ያደረውን ድንጋይ አንሥቶ እንደ ሐውልት አቆመው፤ በዐናቱም ላይ የወይራ ዘይት አፈሰሰበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ያዕቆብም ማልዶ ተነሣ፥ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አድርጎ አቆመው፥ በላዩም ዘይትን አፈሰሰበት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ያዕቆብ በማግሥቱ ጠዋት በማለዳ ተነሣ፤ ተንተርሶት የነበረውንም ድንጋይ መታሰቢያ እንዲሆን እንደ ሐውልት አቆመው፤ በላዩ ላይም የወይራ ዘይት አፈሰሰበት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ያዕ​ቆ​ብም ማልዶ ተነሣ፤ ተን​ተ​ር​ሷት የነ​በ​ረ​ች​ው​ንም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አድ​ርጎ አቆ​ማት፥ በላ​ይ​ዋም ዘይ​ትን አፈ​ሰ​ሰ​ባት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 28:18
16 交叉引用  

አብርሃምም ማልዶ ተነሣ እንጀራንም ወሰደ የውኃ አቁማዳንም ለአጋር በትክሻው አሸከማት ብላቴናውንም ሰጥቶ አስወጣት እርስዋም ሄደች በቤርሳቤህም ምድረ በዳ ተቀበዘበዘች።


አብረሃምም በማለዳ ተነሥቶ አህያውን ጫነ፥ ሁለቱንም ሎሌዎቹንና ልጁን ይስሕቅን ከእርሱ ጋር ወሰደ፥ እንጨትንም ለመሥዋዕት ሰነጠቀ፤ ተነስቶም እግዚአብሔር ወዳለው ቦታ ሄደ።


ወደ አንድ ስፍራም ደረሰ ፀሐይም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ጠልቃ ነበርና ከዚያ አደረ፤ በዚያም ስፍራ ድንጋይ አነሣ ከራሱም በታች ተንተርሶ በዚያ ስፍራ ተኛ።


ሐውልት የቀባህበት በዚያም ለእኔ ስእለት የተሳልህበት የቤቴል አምላክ እኔ ነኝ አሁንም ተነሥተህ ከዚህ አገር ውጣ ወደ ተወለድህበትም ምድር ተመለስ።


ያዕቆብም ድንጋይ ወስዶ ሐውልት አቆመ።


ያዕቆብም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር በተነጋገረበት ቦታ የድንጋይ ሐውልት ተከለ የመጠጥ መሥዋዕትንም በእርሱ ላይ አፈሰሰ ዘይትንም አፈሰሰበት።


ያዕቆብም በመቃብርዋ ላይ ሐውልት አቆመ እርሱም እስከ ዛሬ የራሔል የመቃብርዋ ሐውልት ነው።


አቤሴሎምም ሕያው ሳለ፦ ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም ብሎ ሐውልት ወስዶ በንጉሥ ሸለቆ ውስጥ ለራሱ አቁሞ ነበር፥ ሐውልቱንም በስሙ ጠርቶት ነበር፥ እስከ ዛሬም ድረስ የአቤሴሎም መታሰቢያ ተብሎ ይጠራል።


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


በዚያ ቀን በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ በዳርቻዋም ለእግዚአብሔር አምድ ይሆናል።


እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ማደሪያውን ፈጽሞ ከተከለ በኋላ፥ እርሱንና ዕቃውን ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፥ መሠዊያውንና ዕቃውንም ሁሉ ከቀባና ከቀደሰ በኋላ፤


ኢያሱም የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግሮች በቆሙበት ስፍራ በዮርዳኖስ መካከል ሌሎችን አሥራ ሁለት ድንጋዮች ተከለ፥ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።


ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፥ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።


跟着我们:

广告


广告