Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 28:14 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዘርህ እንደ ምድር አሸዋ ይበዛል፤ በምዕራብና በምሥራቅ፣ በሰሜንና በደቡብ ትስፋፋለህ፤ የምድርም ሕዝቦች ሁሉ በአንተና በዘርህ አማካይነት ይባረካሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ዘርህም እንደ ምድር አሸዋ ይሆናል፥ እስከ ምዕራብና እስከ ምሥራቅ እስከ ሰሜንና እስከ ደቡብ ትስፋፋለህ፥ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በአንተ በዘርህም ይባረካሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ዘርህን እንደ ምድር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ እነርሱ በሁሉ አቅጣጫ ይዞታቸውን ያስፋፋሉ፤ በአንተና በዘርህ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ ይባረካሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ዘር​ህም እንደ ባሕር አሸዋ ይሆ​ናል፤ እስከ ባሕ​ርና እስከ አዜብ እስከ መስ​ዕና እስከ ምሥ​ራቅ ይበ​ዛል፤ ይሞ​ላ​ልም፤ የም​ድ​ርም ሕዝ​ቦች ሁሉ በአ​ንተ፥ በዘ​ር​ህም ይባ​ረ​ካሉ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 28:14
26 交叉引用  

የሚባርኩህንም እባርካለሁ፥ የሚረግሙህንም እረግማለሁ፤ የምድር ነገዶችም ሁሉ በአንተ ይባረካሉ።


ሎጥ ከተለየው በኍላም እግዚአብሔር አብራምን አለው፤


ዓይንህን አንሣና አንተ ካለህበት ስፍራ ወደ ሰሜንና ወደ ደቡብ ወደ ምሥራቅና ወደ ምዕራብ እይ የምታያትን ምድር ሁሉ ለአንተና ለዘርህ ለዘላለም እሰጣለሁና።


ዘርህንም እንደ ምድር አሸዋ አደርጋለሁ፤ የምድርን አሸዋን ይቆጥር ዘንድ የሚችል ስው ቢኖር ዘርህ ደግሞ ይቆጠራል።


አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፤ የምድር አሕዛብም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና።


በእውነት በረከትን እባርክሃለሁ፦ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና በባሕር እንዳል አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶችን ደጅ ይወርሳል፤


የምድር አሕዛብ ሁሉም በዘርህ ይባረካል፦ ቃሌን ሰምተሃልና።


ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ እነዚህንም ምድሮች ሁሉ ለዘርህ ይባረላሉ፤


አንተም፦ በእርግጥ መልካም አደርግልሃለሁ፥ ዘርህንም ከብዛቱ የተንሣ እንድማይቈጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደርጋለሁ ብለህ ነበር።


እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምን የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ በምድርም መካከል ይብዙ።


አባቱም እንቢ አለ እንዲህ ሲል፦ አወቅሁ ልጄ ሆይ አወቅሁ ይህም ደግሞ ሕዝብ ይሆናል ታላቅም ይሆናል ነገር ግን ታናሽ ወንድሙ ከእርሱ ይበልጣል ዘሩም የአሕዛብ ሙላት ይሆናል።


አሁንም፥ አቤቱ አምላክ ሆይ! ቍጥሩ እንደ ምድር ትቢያ በሆነው በብዙ ሕዝብ ላይ አንግሠኸኛልና ለአባቴ ለዳዊት የሰጠኸው ተስፋ ይጽና።


ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለህ፥ ይህችንም የተናገርኋትን ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣታለሁ፥ ለዘላለምም ይወርሱአታል ብለህ በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን እስራኤልንም፥ አስብ።


በቀኝና በግራ ትሰፋፊያለሽና፥ ዘርሽም አሕዛብን ይወርሳልና፥ የፈረሱትንም ከተሞች መኖሪያ ያደርጋልና።


የያዕቆብን ትቢያ ማን ይቈጥራል? የእስራኤልስ እርቦ ማን ይቈጥራል? የጻድቃንን ሞት እኔ ልሙት፥ ፍጻሜዬም እንደ እርሱ ፍጻሜ ትሁን።


እላችኋለሁም፥ ብዙዎች ከምሥራቅና ከምዕራብ ይመጣሉ ከአብርሃምና ከይስሐቅ ከያዕቆብም ጋር በመንግሥተ ሰማያት ይቀመጣሉ፤


እናንተ የነቢያት ልጆችና እግዚአብሔር ለአብርሃም፦ ‘በዘርህ የምድር ወገኖች ሁሉ ይባረካሉ’ ብሎ፥ ከአባቶቻችን ጋር ያደረገው የኪዳን ልጆች ናችሁ።


ለአብርሃምና ለዘሩም የተስፋው ቃል ተነገረ። ስለ ብዙዎች እንደሚነገር፦ ለዘሮቹም አይልም፤ ስለ አንድ እንደሚነገር ግን፦ ለዘርህም ይላል፥ እርሱም ክርስቶስ።


መጽሐፍም እግዚአብሔር አሕዛብን በእምነት እንዲያጸድቅ አስቀድሞ አይቶ፦ በአንተ አሕዛብ ሁሉ ይባረካሉ ብሎ ወንጌልን ለአብርሃም አስቀድሞ ሰበከ።


በክርስቶስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።


አምላክህ እግዚአብሔር እንደ ነገረህ አገርህን ባሰፋ ጊዜ፥ ሰውነትህም ሥጋ መብላት ስለ ወደደች፦ ሥጋ ልብላ ስትል፥ እንደ ሰውነትህ ፈቃድ ሥጋን ብላ።


ዛሬም እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ትጠብቅ ዘንድ፥ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት ደስ የሚያሰኘውን ታደርግ ዘንድ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ቃል ስትሰማ፥ የእግዚአብሔር መቅሠፍት ቁጣ ይመለስ ዘንድ፥ ለአባቶችህም እንደ ማለላቸው ይምርህ ዘንድ፥ ይራራልህም ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ፥ እርም ከሆነው አንዳች ነገር በእጅህ አይንጠልጠልብህ።


የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።


ከዚህ በኋላ አየሁ፥ እነሆም፥ አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


跟着我们:

广告


广告