Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 27:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ያዕቆብም አባቱን አለው፦ የበኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ እንዳዘዝኽኝ አደረግሁ፤ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ ካደንሁትም ብላ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ያዕቆብም አባቱን፣ “እኔ የበኵር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ፤ እስኪ ቀና በልና እንድትመርቀኝ ዐድኜ ካመጣሁት ብላ” አለ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ያዕቆብም አባቱን አለው፦ “የበኩር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፥ እንዳዘዝኸኝ አደረግሁ፥ ነፍስህ ትባርከኝ ዘንድ ቀና በልና ተቀመጥ፥ ካደንሁትም ብላ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ያዕቆብም “የበኲር ልጅህ ዔሳው ነኝ፤ እነሆ፥ እንዳዘዝከኝ አድርጌአለሁ፤ እንድትመርቀኝ እስቲ ቀና በልና ያመጣሁልህን የአደን ሥጋ ተመገብ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ያዕ​ቆ​ብም አባ​ቱን አለው፥ “የበ​ኵር ልጅህ እኔ ዔሳው ነኝ፤ እን​ዳ​ዘ​ዝ​ኸኝ አደ​ረ​ግሁ፤ ነፍ​ስህ ትባ​ር​ከኝ ዘንድ ቀና ብለህ ተቀ​መጥ፤ ካደ​ን​ሁ​ትም ብላ።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 27:19
15 交叉引用  

በፊትም የወጣው ቀይ ነበረ፥ ሁለንትናውም ጠጕር ለብሶ ነበር፤ ስሙም ዔሳው ተባለ።


ይስሐቅም ዔሳውን ይወድ ነበረ ካደነው ይበላ ነበርና፤ ርብቃ ግን ያዕቆብን ትወድ ነበረች።


ወደ አባቱም ገብቶ፦ አባቴ ሆይ አለው እርሱም፦ እነሆኝ፤ ልጄ ሆይ አንተ ማን ነህ? አለ።


ይስሐቅም ያዕቆብን፦ ልጄ ሆይ አንተ ልጄ ዔሳ እንደ ሆንህ ወይም እንዳልሆንህ እዳስስህ ዘንድ ቅረበኝ አለው።


እርሱም ደግሞ ጣፋጭ መብል አዘጋጀ ለአባቱም አገባ አባቱንም፦ አባቴ ይነሣ ነፍስህም ትባርከኝ ዘንድ ከልጁ አደን ይብላ አለው።


እርሱም፦ ወንድምህ በተንኮል ገብቶ በረከትህን ወሰደብህ አለ።


ሳልሞትም ነፍሴ እንድትባርክህ የጣፈጠ መብል እኔ እንደምወደው አዘጋጅትህ እበላ ዘንድ አምጣልኝ።


የወንድምህ ቍጣ ከአንተ እስኪመለስ ድረስ፥ ያደረግህባትንም እስኪረሳው ድረስ ከዚይም ልኬ አስመጣሃለሁ በአንድ ቀን ሁለታችሁን ለምን አጣለሁ?


እርሱም “እኔ ደግሞ እንደ አንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም ‘እንጀራ ይበላ ዘንድ ውሃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው፤’ ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ፤” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።


ኢዮርብዓምም ሚስቱን “ተነሺ፤ የኢዮርብዓምም ሚስት እንደ ሆንሽ እንዳትታወቂ ልብስሽን ለውጪና ወደ ሴሎ ሂጂ፤ እነሆ፥ በዚህ ሕዝብ ላይ እንድነግሥ የነገረኝ ነቢዩ አኪያ በዚያ አለ።


እናንተም፦ ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፥ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፥ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም ስላላችሁ፥


跟着我们:

广告


广告