Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 26:7 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት እርሱም፦ እኅቴ ናት አለ የዚያም ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና እርስዋ ውብ ነበረችና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 የዚያም አገር ሰዎች ስለ ሚስቱ በጠየቁት ጊዜ፣ “እኅቴ ናት” አለ፤ ምክንያቱም፣ “ሚስቴ ናት ብል ርብቃ ቈንጆ ስለ ሆነች፣ ያገሬው ሰዎች በርሷ ምክንያት ይገድሉኛል” በማለት ፈርቶ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት፥ እርሱም፦ “እኅቴ ናት” አለ፥ የዚያም ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና፥ እርሷ ውብ ነበረችና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የዚያ አገር ሰዎችም ስለ ርብቃ “ምንህ ናት” ብለው በጠየቁት ጊዜ “እኅቴ ናት” አላቸው፤ ይህንንም ያለበት ምክንያት ርብቃ በጣም ቈንጆ ስለ ነበረች የዚያ አገር ሰዎች በእርስዋ ሰበብ እንዳይገድሉት በመፍራት ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 የዚህ ስፍራ ሰዎች ለር​ብቃ ሲሉ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ እር​ስ​ዋም ውብ ነበ​ረ​ችና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 26:7
15 交叉引用  

ወደ ግብፅም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤


እንግዲህ በአንቺ ምክንያት መልካም ይሆንልኝ ዘንድ ስለ አንቺም ነፍሴ ትድን ዘንድ፥ እኅቱ ነኝ በዩ።


የፈርዖንም አለቆች አዩአት በፈርዖንም ፊት አመስመገኑአት ሴቲቱንም ወደ ፈርዖን ቤት ወሰዱአት።


አብርሃምም አለ፤ በዚህ ስፍራ እግዚአብሔርን መፍራት በእውነት እንድሌለ ለሚስቴም ሲሉ እንደሚገድሉኝ ስላሰብሁ ነው።


አብርሃምም ሚስቱን ሣራም፤ እኅቴ ናት አለ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት።


እኅቴ ናት ያለኝ እርሱ አይደለምን? እርስዋም ደግሞ ራስዋ ወንድሜ ነው አለች፤ በልቤ ቅንነትና በእጄ ንጽሕነት ይህንን አደረግሁ።


ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ ወንድ የማያውቃት ድንግልም ነበረች፤ ወደ ምንጭም ወረደች እንስራዋንም ሞላች ተመልሳም ወጣች።


ይስሐቅም በጌራራ ተቀመጠ።


በዚያም ብዙ ቀን ከተቀመጠ በኍላ የፍልስጥኤም ንጉሥ አቢሜሌም በመስኮት ሆኖ ጎበኘ፥ ይስሐቅም ሚስቱን ርብቃን ሲዳራት አየ።


ልያም ዓይነ ልም ነበረች፤ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች ፊትዋም ውብ ነበረ።


ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ።


ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤


እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥


跟着我们:

广告


广告