Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 25:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ልጆችም በሆድዋ ውስጥ ይገፋፋ ነበር፤ እርስዋም፦ እንዲህ ከሆነ ይህ ለእኔም ምኔ ነው? አለች። ከእግዚአብሔርም ትጠይቅ ዘንድ ሄደች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ልጆቹም በማሕፀኗ ውስጥ እርስ በርሳቸው ይጋፉ ጀመር፤ እርሷም “ለምን እንዲህ ይሆንብኛል?” ብላ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሄደች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ልጆቹም በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋፉ ነበር፤ እርሷም፥ “እንዲህ እሆን ዘንድ ከሆነ፥ ስለምንድን ነው የምኖረው?” አለች። ከጌታም ምላሽ ታገኝ ዘንድ ሄደች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የተፀነሱትም መንትያዎች ስለ ነበሩ እርስ በርሳቸው በማሕፀንዋ ውስጥ ይገፋፉ ነበር፤ እርስዋም “ይህን ዐይነት ነገር ለምን ደረሰብኝ?” በማለት ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ተነሣሣች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ልጆ​ች​ዋም በሆ​ድዋ ውስጥ ይን​ቀ​ሳ​ቀሱ ነበር ፤ እር​ስ​ዋም፥ “እን​ዲህ እሆን ዘንድ ካለኝ ይህ ለእኔ ምኔ ነው?” አለች። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትለ​ምን ዘንድ ሄደች።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 25:22
7 交叉引用  

ቍርባናችሁን ባቀረባችሁ ጊዜ፥ ልጆቻችሁንም በእሳት ባሳለፋችሁ ጊዜ፥ እስከ ዛሬ ድረስ በጣዖቶቻችሁ ትረክሳላችሁን የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ከእናንተስ ዘንድ እጠየቃለሁን? እኔ ሕያው ነኛና ከእናንተ ዘንድ አልጠየቅም፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለዚህ ደግሞ አደግላቸው ዘንድ የእስራኤል ቤት ይሹኛል ሰውንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።


ከእግዚአብሔርም፦ ገና ወደዚህ የሚመጣ ሰው አለን? ብለው ደግሞ ጠየቁት እግዚአብሔርም፦ እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል ብሎ መለሰ።


በውኑ ስለ እርሱ እግዚአብሔርን እጠይቅ ዘንድ ዛሬ ጀመርሁን? ይህ ከእኔ ይራቅ፥ እኔ ባሪያህ ይህን ሁሉ እጅግ ወይም ጥቂት ቢሆን አላውቅምና ንጉሡ እንደዚህ ያለውን ነገር በእኔ በባሪያውና በአባቴ ቤት ሁሉ ላይ አያኑር አለ።


ሳኦልም እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እግዚአብሔርም በሕልም ወይም በኡሪም ወይም በነቢያት አልመለሰለትም።


ዳዊትም፦ የእነዚህን ሠራዊት ፍለጋ ልከተልን? አገኛቸዋለሁን? ብሎ እግዚአብሔርን ጠየቀ፥ እርሱም፦ ታገኛቸዋለህና፥ ፈጽመህም ምርኮውን ትመልሳለህና ፍለጋቸውን ተከተል ብሎ መለሰለት።


ዛሬ ነቢይ የሚባለው ቀድሞ ባለ ራእይ ይባል ነበርና አስቀድሞ በእስራኤል ዘንድ ሰው እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ሲሄድ፦ ኑ፥ ወደ ባለ ራእይ እንሂድ ይል ነበር።


跟着我们:

广告


广告