Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 24:40 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 እርሱም አለኝ፦ አካሄዴን በፊቱ ያደረግ ሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል መንገድህንም ያቀናም፤ ለልጄም ከወገኖቼ ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 “እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁ እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋራ ይልካል፤ ከገዛ ወገኖቼና ከአባቴ ቤት፣ ለልጄ ሚስት እንድታመጣለት መንገድህን ያቃናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 እርሱም አለኝ፦ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፥ መንገድህንም ያቀናል፥ ለልጄም ከወገኖቼ ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 እርሱም እንዲህ አለኝ ‘ዘወትር የማገለግለው እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፤ ጒዞህም የተቃና እንዲሆን ያደርጋል፤ በዚህ ሁኔታ አንተም ከአባቴ ቤተሰብና ከዘመዶቼ መካከል ለልጄ ሚስት ልታጭለት ትችላለህ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እር​ሱም አለኝ፦ አካ​ሄ​ዴን በፊቱ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ከአ​ንተ ጋር ይል​ካል። መን​ገ​ድ​ህ​ንም ያቀ​ናል፤ ለል​ጄም ከወ​ገ​ኖች ከአ​ባ​ቴም ቤት ሚስ​ትን ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 24:40
20 交叉引用  

አብራምም የዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሰው በሆን ጊዜ እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና፥ እነሆ ኤልሻዳይ ነኝ በፊቴ ተመላለስ፥ ፍጽምም ሁን፤


እርሱም፦ እግዚአብሔር መንገዴን አቅንቶልኛልና አታዘግዩኝ፤ ወደ ጌታዬ እሄድ ዘንድ አሰናብቱኝ አላቸው።


ከአባቴ ቤት ከተወለድሁባት ምድርም ያወጣኝ፦ ይህችንም ምድር እሰጥሃለሁ ብሎ የነገረኝና የመለልኝ የሰማይ አምላክ እግዚአብሔር እርሱ መልአኩን በፊትህ ይሰድዳል ከዚያም ከልጄ ሚስትን ትወስዳለህ።


ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከው እንዲህም አለ፦ አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ ዛሬ ድርስ እኔን የመገባኝ እግዚአብሔር ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር ከክፋ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እርሱ


ማቱሳላንም ከወለደ በኍላ የኖረው ሁለት መቶ ዓመት ሆነ ወለደ።


ሄኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ወስዶታልና።


የኖኅ ትውልድ እንዲህ ነው። ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ስው ነበረ ኖኅ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረግ።


በርታ፤ ሰውም ሁን፤ የምታደርገውንና የምትሄድበትን ሁሉ ታከናውን ዘንድ፥ በሙሴ ሕግ እንደ ተጻፈ ሥርዐቱንና ትእዛዛቱን ፍርዱንና ምስክሩንም ትጠብቅ ዘንድ፥ በመንገዱም ትሄድ ዘንድ፥ የአምላክህን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቅ።


ሰሎሞንም አለ “እርሱ በፊትህ በእውነትና በጽድቅ በልብም ቅንነት ከአንተ ጋር እንደ ሄደ፥ ከባሪያህ ከአባቴ ከዳዊት ጋር ታላቅ ቸርነት አድርገሃል፤ ዛሬ እንደ ሆነም በዙፋኑ ላይ የሚቀመጥ ልጅ ሰጥተህ ታላቁን ቸርነትህን አቆይተህለታል።


እንዲህም አለ “የእስራኤል አምላክ አቤቱ! በላይ በሰማይ በታችም በምድር አንተን የሚመስል አምላክ የለም፤ በፍጹም ልባቸው በፊትህ ለሚሄዱ ባሪያዎችህ ቃል ኪዳንንና ምሕረትን የምትጠብቅ፥


“አቤቱ፥ በፊትህ በእውነትና በፍጹም ልብ እንደ ሄድሁ፥ ደስ የሚያሰኝህንም እንዳደረግሁ ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ።” ሕዝቅያስም እጅግ አድርጎ አለቀሰ።


በመንገድ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ስፍራ ያገባህ ዘንድ፥ እነሆ፥ እኔ መልአክን በፊትህ እሰድዳለሁ።


ናቡከደነፆርም መልሶ፦ መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፥ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብድናጎም አምላክ ይባረክ።


ከቶ ለማን ብሎአል? ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን?


እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።


ይህንም ያየሁትና የሰማሁት እኔ ዮሐንስ ነኝ። በሰማሁትና ባየሁትም ጊዜ ይህን ባሳየኝ በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ።


跟着我们:

广告


广告