Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 24:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ ወንድ የማያውቃት ድንግልም ነበረች፤ ወደ ምንጭም ወረደች እንስራዋንም ሞላች ተመልሳም ወጣች።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ልጃገረዲቱ እጅግ ውብና ወንድ ያላወቃት ድንግል ነበረች። ወደ ምንጩም ወርዳ ውሃ በእንስራዋ ሞልታ ተመለሰች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ብላቴናይቱም መልክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማያውቃት ድንግልም ነበረች፥ ወደ ምንጭም ወረደች እንስራዋንም ሞላች፥ ተመልሳም ወጣች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ርብቃ ገና ወንድ ያልደረሰባት በጣም ቈንጆ ልጃገረድ ነበረች፤ እርስዋ ወደ ውሃው ጒድጓድ ወርዳ በእንስራዋ ውሃ ከቀዳች በኋላ ተመለሰች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ብላ​ቴ​ና​ይ​ቱም መል​ክዋ እጅግ ያማረ፥ ወንድ የማ​ታ​ውቅ ድን​ግል ነበ​ረች። ወደ ውኃው ጕድ​ጓ​ድም ወረ​ደች፤ ውኃም ቀዳች፤ እን​ስ​ራ​ዋ​ንም ሞልታ ወጣች።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 24:16
7 交叉引用  

ወደ ግብፅም ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፤ አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤


የዚያም ስፍራ ሰዎች ስለ ሚስቱ ጠየቁት እርሱም፦ እኅቴ ናት አለ የዚያም ስፍራ ስዎች ለርብቃ ሲሉ እንዳይገድሉኝ ብሎ ሚስቴ ናት ማለትን ፈርቶአልና እርስዋ ውብ ነበረችና።


ልያም ዓይነ ልም ነበረች፤ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች ፊትዋም ውብ ነበረ።


ያለውንም ሁሉ ለዮሴፍ አስረከበ ከሚበላውም እንጀራ በቀር ምንም የሚያውቀው አልነበረም። የዮሴርም ፊቱ መልከ መልካምን ውብ ነበረ።


አዳምም ሚስቱን ሔዋንን አወቀ ፀነሰችም፤ ቃየንንም ወለደች። እርስዋም ወንድ ልጅ ከእግዚአብሔር አገኘሁ አለች።


እኔ ተኝቻለሁ፥ ልቤ ግን ነቅቶአል፥ የውዴ ቃል ነው፥ እርሱም ደጁን ይመታል፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደምደሚያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቈንዳላዬም የሌሊት ነጠብጣብ ሞልቶበታልና ክፈችልኝ።


跟着我们:

广告


广告