Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 23:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በእርሻው ዳር ያለውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን በሙሉ ዋጋ በመካከላችሁ ይስጠኝ፥ መቃብሩ የእኔ ርስት እንዲሆን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ይኸውም በዕርሻው ድንበር ላይ ያለችውን መክፈላ የተባለችውን ዋሻውን እንዲሸጥልኝ ነው፤ በመካከላችሁም የመቃብር ቦታ እንድትሆነኝ በሙሉ ዋጋ እንዲሸጥልኝ ለምኑልኝ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በእርሻው ዳር ያለውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻውን ይስጠኝ፥ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንዲሰጠኝ አድርጉልኝ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በእርሻው ድንበር ላይ ያለችውን ማክፌላ የተባለችውን ድርብ ክፍል ያላትን ዋሻ እንዲሸጥልኝ ጠይቁልኝ፤ ይህ ስፍራ የመቃብር ቦታ እንዲሆንልኝ በእናንተ ፊት ሙሉ ዋጋ ከፍዬ እንድገዛው አድርጉልኝ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 በእ​ር​ሻው ዳር ያለ​ች​ውን ድርብ ክፍል ያላ​ትን ዋሻ​ውን ይስ​ጠኝ፤ መቃ​ብሩ የእኔ ርስት እን​ዲ​ሆን በሚ​ገ​ባው ዋጋ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ይስ​ጠኝ፤ ከእ​ር​ሱም እገ​ዛ​ለሁ።”

参见章节 复制




ዘፍጥረት 23:9
10 交叉引用  

ኤፍሮን፥ በኬጢ ሰው ኤፍሮን፥ የኬጢ ልጆችና ወደ ከተማ የሚገቡ ሁሉ ሲሰሙ


ለኬጢ ልጆችም እንዲህ ሲል ተናገረ፦ እኔ በእናንተ ዘንድ ስደተኛና መጻተኛ ነኝ በእናንተ ዘንድ የመቃብር ርስት ስጡኝ፥ ሬሳዬንም ከፊቴ ልቅበር።


እንዲህም አላቸው፦ ሬሳዬን ከፊቴ እንድቀብር ከወደዳችሁስ ስሙኝ ከሰዓር ልጅ ከኤፍሮንም ለምኑልኝ፤


አብርሃምም ከኬጢ ልጆች የገዛው እርሻ ይህ ነው አብርሃምና ሚስቱ ሣራ ከዚያ ተቀበሩ።


እንዲህ ብሎም አዘዛቸው፦ እኔ ወደ ወገኖቼ እሰበሰባለሁ በኬጢያዊ በኤፍሮን እርሻ ላይ ባለችው ዋሻ ከአባቶቼ ጋር ቅበሩኝ


ልጆቹም ወደ ከነዓን ምድር አጓዙት ባለ ሁለት ክፍል በሆነች ዋሻም ቀበሩት እርስዋም በመምሬ ፊት ያለች አብርሃም ለመቃብር ርስት ከኬጡያዊ ከኤፍሮን ከእርሽ ጋር የገዛት ዋሻ ናት


ዳዊትም ኦርናን “በላዩ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እሠራ ዘንድ ይህን የአውድማ ስፍራ ስጠኝ፤ በሙሉ ዋጋ ስጠኝ፤ መቅሰፍቱም ከሕዝቡ ይከለከላል” አለው።


ንጉሡም ዳዊት ኦርናን “አይደለም፤ ነገር ግን ለአንተ ያለውን ለእግዚአብሔር አምጥቼ የሚቃጠል መሥዋዕት በከንቱ አላቀርብምና በሙሉ ዋጋ እገዛዋለሁ፤” አለው።


ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።


እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።


跟着我们:

广告


广告