ዘፍጥረት 23:16 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 አብርሃምም፣ ኤፍሮን በኬጢያውያን ፊት በተናገረው ዋጋ ተስማማ፤ በወቅቱም የንግድ መለኪያ መሠረት አራት መቶ ጥሬ ብር መዘነለት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 አብርሃምም ከኤፍሮን ጋር ተስማማ፥ በሒታውያንም ልጆች ፊት የነገረውን አራት መቶ ሰቅል በነጋዴዎች ሚዛን ልክ መዝኖ አብርሃም ለኤፍሮን ሰጠው፥ ብሩም ለመሸጫ ለመለወጫ የሚተላለፍ ነበረ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 አብርሃምም በነገሩ ተስማምቶ ዔፍሮን በሕዝቡ ፊት በተናገረው መሠረት በነጋዴዎች ሚዛን ልክ አራት መቶ ብር መዝኖ ሰጠው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 አብርሃምም የኤፍሮንን ነገር ሰማ፤ አብርሃምም በኬጢ ልጆች ፊት የነገረውንና ተቀባይነት ያለውን ግብዝ ያይደለ አራት መቶ ምዝምዝ ብር መዝኖ ለኤፍሮን ሰጠው። 参见章节 |