Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 21:22 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፤ በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በዚያ ጊዜ አቢሜሌክ ከሰራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋራ ሆኖ አብርሃምን እንዲህ አለው፤ “በምታደርገው ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋራ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በዚያም ዘመን አቢሜሌክ ከሙሽራው ወዳጅ ከአኮዘትና ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር አብርሃምን አለው፦ “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፥

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 በዚያን ጊዜ አቤሜሌክ ከሠራዊቱ አለቃ ከፊኮል ጋር ሄደና አብርሃምን “በምታደርገው ሁሉ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 በዚያ ዘመን አቤ​ሜ​ሌክ፥ ሚዜው አኮ​ዘ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብ​ር​ሃም ሄደው አሉት፥ “በም​ታ​ደ​ር​ገው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 21:22
22 交叉引用  

አቢሜሌክም በጎችንና ላሞችን ወንዶችና ሴቶች ባሪያዎችን አመጣ፤ ለአብርሃምም ስጠው ሚስቱን ሣራንም መለሰለት።


አብርሃምም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ እግዚአብሔርም አቢሜሌክን ሚስቱንም ባሪያዎቹንምም ፈውሳቸው


አብርሃምም ሚስቱን ሣራም፤ እኅቴ ናት አለ የጌራራ ንጉሥ አቢሜሌክም ላከና ሣራን ወሰዳት።


አቢሜሌክና የሙሽራው ወዳጅ አኮዘት የሠራዊቱም አለቃ ፊኮል ከጌራራ ወደ እርሱ ሄዱ።


እነርሱም አሉት፦ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ በእርግጥ አየን፤


እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ በምትሄድባትም ምድር እመልስሃለሁ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድርስ አልተውህምና።


ላባም፦ በዓይንህ ፊት ሞገስን የማገኝ ብሆንስ ከዚህ ተቀመጥ፤ እግዚአብሔር በአንተ ምክንያት እንደ ባረከኝ ተመልክቼአለሁና አለው።


እንዲህም አላቸው፦ የአባታችሁ ፊት ከእኔ ጋር እንደ ዱሮ እንዳልሆን አያለሁ ነገር ግን የአባቴ አምላክ ከእኔ ጋር ነው።


ወደ ጢሮስም ምሽግ ወደ ኤዊያውያንና ወደ ከነዓናውያንም ከተሞች ሁሉ መጡ፥ በይሁዳም ደቡብ በኩል በቤርሳቤህ ወጡ።


የዳዊት ልጅ ሰሎሞንም በመንግሥቱ በረታ፤ አምላኩም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረ፤ እጅግም አገነነው።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የግብፅ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፥ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፥ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።


ተመካከሩ፥ ምክራችሁ ይፈታል፥ ቃሉን ተናገሩ፥ ቃሉም አይጸናም፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።


የሠራዊትም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዚያ ዘመን ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ አሥር ሰዎች የአንዱን አይሁዳዊ ሰው ልብስ ዘርፍ ይዘው፦ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር እንዳለ ሰምተናልና ከእናንተ ጋር እንሂድ ይላሉ።


እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፥ ትርጓሜውም፦ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው።


እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


በልቡም የተሰወረ ይገለጣል እንዲሁም፦ እግዚአብሔር በእውነት በመካከላቸው ነው ብሎ እየተናገረ በፊቱ ወድቆ ለእግዚአብሔር ይሰግዳል።


አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፥ ያላችሁም ይብቃችሁ፤ እርሱ ራሱ፦ አልለቅህም ከቶም አልተውህም ብሎአልና፤


እግዚአብሔርም ኢያሱን፦ ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ዓይን ከፍ ከፍ አደርግህ ዘንድ እጀምራለሁ።


እነሆ፥ አይሁድ ሳይሆኑ፦ አይሁድ ነን ከሚሉ ነገር ግን ከሚዋሹ ከሰይጣን ማኅበር አንዳንዶችን እሰጥሃለሁ እነሆ፥ መጥተው በእግሮችህ ፊት ይሰግዱ ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ።


ዳዊትም ለሳኦል ማለለት፥ ሳኦልም ወደ ቤቱ ሄደ፥ ዳዊትና ሰዎቹም ወደ አምባው ወጡ።


ሳሙኤልም አደገ፥ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ፥ ከቃሉም አንዳች በምድር ላይ አይወድቀም ነበር።


跟着我们:

广告


广告