Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 21:21 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 በፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ፤ እናቱም ከምድረ ግብፅ ሚስት ወሰደችለት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 በፋራን ምድረ በዳ ሳለም፣ እናቱ ከግብጽ አንዲት ሴት አምጥታ አጋባችው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 በፋራን ምድረ በዳም ተቀመጠ፥ እናቱም ከምድረ ግብጽ ሚስት ወሰደችለት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እናቱም ከአንዲት ግብጻዊት ጋር አጋባችው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በፋ​ራን ምድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ እና​ቱም ከም​ድረ ግብፅ ሚስት ወሰ​ደ​ች​ለት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 21:21
18 交叉引用  

የሖር ሰዎችንም በሴይር ተራራቸው በበረሀ አጠገብ እስካለች እስከ ኤል ፋራን ድረስ መቱ።


አብራምም የሦራን ቃል ሰማ። አብራምም በከነዓን ምድር አሥር ዓመት ከተቀመጠ በኍላ፤ የአብራም ሚስት ሦራ ግብፃዊት ባሪያዋን አጋርን ወስዳ ለባልዋ ለአብራም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠችው።


መኖሪያቸውም ከኤውላጥ አንሥቶ በግብፅ ፊት ለፊት እስከምትገኝ እስከሱር ድረስ ወደ አሦር በምትወስደው መንገድ ላይ ነበረ፤ እንዲህም በወንድሞቹ ሁሉ ፊት ተቀመጠ።


ርብቃም ይስሐቅን አለችው፦ ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተነሣ ሕይወቴን ጠላሁት ያዕቆብ ከዚህ አገር ሴቶች ልጆች ሚስትን የሚያገባ ከሆነ በሕይወት መኖር ለምኔ ነው?


ከምድያምም ተነሥተው ወደ ፋራን መጡ፤ ከእነርሱም ጋር ከፋራን ሰዎች ወሰዱ፤ ወደ ግብጽም መጡ፤ ወደ ግብጽም ንጉሥ ወደ ፈርዖን ዘንድ ገቡ፤ እርሱም ቤት ሰጥቶ ቀለብ ዳረገው፤ ምድርም ሰጠው።


ዮዳሄም ሁለት ሚስቶች አጋባው፤ ወንዶችና ሴቶችም ልጆችንም ወለደ።


ተጋቡ ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ውለዱ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፥ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶችን ልጆች ይውለዱ፥ ከዚያም ተባዙ ጥቂቶችም አትሁኑ።


እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።


የእስራኤልም ልጆች ከሲና ምድረ በዳ በየጉዞአቸው ተጓዙ፤ ደመናውም በፋራን ምድረ በዳ ቆመ።


ከዚያም በኋላ ሕዝቡ ከሐጼሮት ተጓዙ፥ በፋራንም ምድረ በዳ ሰፈሩ።


በፋራን ምድረ በዳና በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ ሄደው ደረሱ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።


ሙሴም እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከፋራን ምድረ በዳ ላካቸው፤ እነርሱም ሁሉ የእስራኤል ልጆች አለቆች ነበሩ።


እንዲሁም ድንግልን ያገባ መልካም አደረገ ያላገባም የተሻለ አደረገ።


ወጥቶም ለአባቱና ለእናቱ፦ በተምና ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አይቻለሁ፥ አሁንም እርስዋን አጋቡኝ አላቸው።


ሳሙኤልም ሞተ፥ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ።


跟着我们:

广告


广告