Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 2:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እግዚአብሔር አምላክም ለማየት ደስ የሚያስኘውን፤ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፤ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እግዚአብሔር አምላክም ለዐይን የሚያስደስት ለመብልም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፤ በአትክልቱ ቦታ መካከልም የሕይወት ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም መልካምና ክፉን መለየት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በዚያም፥ ጌታ እግዚአብሔር ለማየት ደስ የሚያሰኘውን፥ ለመብላትም መልካም የሆነውን ዛፍ ሁሉ ከምድር አበቀለ፥ በገነትም መካከል የሕይወትን ዛፍ፥ መልካምንና ክፉን የሚያስታውቀውንም ዛፍ አበቀለ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 በዚያም ለዐይን የሚያስደስቱና ለምግብነት የሚጠቅሙ ልዩ ልዩ ዛፎች እንዲበቅሉ አደረገ፤ ደግሞም በአትክልቱ ቦታ መካከል ሕይወት የሚሰጥ ዛፍ ነበረ፤ እንዲሁም ደጉን ከክፉ ለመለየት የሚያስችል ዕውቀት የሚሰጥ ሌላ ዛፍ ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ለማ​የት ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን፥ ለመ​ብ​ላ​ትም መል​ካም የሆ​ነ​ውን ዛፍ ሁሉ ደግሞ ከም​ድር አበ​ቀለ፤ በገ​ነ​ትም መካ​ከል የሕ​ይ​ወ​ትን ዛፍ፥ መል​ካ​ም​ንና ክፉን የሚ​ያ​ሳ​የ​ው​ንና የሚ​ያ​ስ​ታ​ው​ቀ​ው​ንም ዛፍ አበ​ቀለ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 2:9
19 交叉引用  

ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።


እግዚአብሔር አምላክም አለ፤ እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኚ እንደ አንዱ ሆኑ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘጋ፤ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፤ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር፤


አዳምንም አስወጣው፤ ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልበል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ።


ነገር ግን በገነት መካክል ካለው ከዛፉ ፍሬ፤ እግዚአብሔር አለ፤ እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም።


ከእርስዋ በበላችሁ ቀን ዓይኖቻችሁ እንዲከፈቱ እንደ እግዚአብሔርም መልካምንና ክፉን የምታውቁ እንድትሆኑ እግዚአብሔር ስለሚያውቅ ነው እንጂ።


የሐሰተኞችን ምልክት ከንቱ አደርጋለሁ፥ ምዋርተኞችንም አሳብዳለሁ፥ ጥበበኞቹንም ወደ ኋላ እመልሳለሁ እውቀታቸውንም ስንፍና አደርጋለሁ፥


በክፋትሽ ታምነሻል፥ የሚያየኝ የለም ብለሻል፥ ጥበብሽና እውቀትሽ አታልለውሻል፥ በልብሽም፦ እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ብለሻል።


ወደ ጕድጓድ ከሚወርዱ ጋር ወደ ሲኦል በጣልሁት ጊዜ ከመውደቁ ድምፅ የተነሣ አሕዛብን እንቀጠቀጥሁ፥ ውኃም የሚጠጡ ሁሉ፥ ምርጦችና መልካካሞች የሊባኖስ ዛፎች፥ የዔድን ዛፎች ሁሉ በታችኛው ምድር ውስጥ ተጽናንተዋል።


በክብርና በታላቅነት በዔድን ዛፎች መካከል ማንን መስለሃል? ነገር ግን ከዔድን ዛፎች ጋር ወደ ታችኛው ምድር ያወርዱሃል፥ በሰይፍም በተገደሉት ባልተገረዙት መካከል ትተኛለህ። ይህም ፈርዖንና የሕዝቡ ብዛት ሁሉ ነው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


በወንዙም አጠገብ በዳሩ ላይ በዚህና በዚያ ፍሬው የሚበላ ዛፍ ሁሉ ይበቅላል፥ ቅጠሉም አይረግፍም ፍሬውም አይጐድልም፥ ውኃውም ከመቅደስ ይወጣልና በየወሩ ሁሉ የፍሬ በኵር ያገኛል፥ ፍሬውም ለመብል ቅጠሉም ለመድኃኒት ይሆናል።


የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ።


ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል።


እርሱም እንዳዘዘን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እናደርጋት ዘንድ ይህችን ትእዛዝ ሁሉ ብንጠብቅ ለእኛ ጽድቅ ይሆንልናል።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ። ድል ለነሣው በእግዚአብሔር ገነት ካለው ከሕይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ።


ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።


በወንዙም ወዲያና ወዲህ በየወሩ እያፈራ አሥራ ሁለት ፍሬ የሚሰጥ የሕይወት ዛፍ ነበረ፥ የዛፉም ቅጠሎች ለሕዝብ መፈወሻ ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告