Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 19:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እነርሱም፤ ወዲያ ሂድ አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፤ ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን። ሎጥንም እጅግ ተጋፉት የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እነርሱም፣ “ዞር በል! ይህ ሰው ራሱ ትናንት ተሰድዶ የመጣ ነው፤ ዛሬ ደግሞ ዳኛ ልሁን ይላል። ዋ! በእነርሱ ካሰብነው የከፋ እንዳናደርስብህ!” አሉት፤ ከዚያም ሎጥን እየገፈታተሩ የበሩን መዝጊያ ለመስበር ተንደረደሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 እነርሱም፦ “ወዲያ ሂድ” አሉት። ደግሞም እንዲህ አሉ፦ “ይህ ሰው በእንግድነት ለመኖር መጣ፥ ፍርዱንም ይፈርድ ዘንድ ይፈልጋል፥ አሁን በአንተ ከእነርሱ ይልቅ ክፉ እናደርግብሃለን።” ሎጥንም እጅግ ተጋፉት፥ የደጁንም መዝጊያ ለመስበር ቀረቡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሰዎቹ ግን “አንተ ስደተኛ፥ ሂድ ወዲያ! ለመሆኑ ልናደርገው የሚገባንን ነገር የምትነግረን አንተ ማን ነህ? ሂድ ወዲያ፤ አለበለዚያ በእነርሱ ላይ ልናደርግ ካሰብነው የከፋ ነገር በአንተ ላይ እናደርጋለን” አሉት። በዚህ ዐይነት ሎጥን ወዲያ ገፍትረው በሩን ለመስበር ተነሣሡ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እነ​ር​ሱም፥ “ወዲያ ሂድ፤ ከእኛ ጋር ልት​ኖር መጣህ እንጂ ልት​ገ​ዛን አይ​ደ​ለም፤ አሁ​ንም ከእ​ነ​ርሱ ይልቅ አን​ተን እና​ሠ​ቃ​ይ​ሃ​ለን” አሉት።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 19:9
21 交叉引用  

እግዚአብሔርም አለ፤ እነሆ እነርሱ አንድ ቋንቋ አላቸው፤ ይህንም ለማድረግ ጀመሩ፤ አሁንም ያሰቡትን ሁሉ ለመሥራት አይከለከሉም።


አብራም በከነዓን ምድር ተቀመጠ ሎጥም በአገሩ ሜድ ባሉት ከተሞች ተቀመጠ፥ እስከ ስዶም ሰዎች ድረስ ድንኳኑን አዘዋወረ።


ያም፦ “በእኛ ላይ አንተን አለቃ ወይስ ዳኛ ማን አደረገህ? ወይስ ግብፃዊውን እንደገደልኸው ልትገድለኝ ትሻለህን?” አለው። ሙሴም፦ “በእውነት ይህ ነገር ታውቆአል” ብሎ ፈራ።


የአፉ ቃል መጀመሪያ ስንፍና ነው፥ የንግግሩ ፍጻሜም ክፉ እብደት ነው።


አንድ ድርሻ ሁሉን እንዲያገኝ ከፀሐይ በታች በተደረገው ሁሉ ይህ ነገር ክፉ ነው፥ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ ክፋትን ትሞላለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ነው፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።


እነርሱም፦ ለራስህ ቁም፥ እኔ ከአንተ ይልቅ ቅዱስ ነኝና ወደ እኔ አትቅረብ ይላሉ፥ እነዚህ በአፍንጫዬ ዘንድ ጢስ ቀኑንም ሁሉ የምትነድድ እሳት ናቸው።


ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፥ የኋለኛውም ዝናብ ጠፋ፥ የጋለሞታም ሴት ፊት ነበረብሽ፥ ታፍሪም ዘንድ እንቢ ብለሻል።


ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፥ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፥ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።


አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፥ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፥ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።


እነሆ፥ የእኅትሽ የሰዶም ኃጢአት ይህ ነበር፥ ትዕቢት እንጀራን መጥገብ መዝለልና ሥራ መፍታት በእርስዋና በሴቶች ልጆችዋ ነበረ፥ የችግረኛውንና የድሀውንም እጅ አላጸናችም።


በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።


ፍልስጥኤማዊውም ዳዊትን፦ ወደ እኔ ና፥ ሥጋህንም ለሰማይ ወፎችና ለምድር አራዊት እሰጣለሁ አለው።


ሰውዮውም፦ አስቀድሞ ስቡን ያቃጥሉት ኋላም ሰውነትህ ደስ የሚያሰኛትን ትወስዳለህ ቢለው፥ እርሱ፦ አይሆንም፥ ነገር ግን አሁን ስጠኝ፥ እንቢም ብትል በግድ እወስደዋለሁ ይለው ነበር።


ስለዚህም በጌታችንና በቤቱ ሁሉ ላይ ክፉ ነገር እንዲመጣ ተቆርጦአልና፥ እርሱ ምናምንቴ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊናገረው አይችልምና የምታደርጊውን ተመልከቺና እወቂ።


跟着我们:

广告


广告