Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 19:29 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፤ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚይ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 እንደዚህ አድርጎ እግዚአብሔር በረባዳው ስፍራ የነበሩትን ከተሞች ሲያጠፋ አብርሃምን ዐሰበው፤ ስለዚህም የሎጥ መኖሪያ የነበሩትን ከተሞች ካጠፋው መዓት ሎጥን አወጣው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 እግዚአብሔርም እነዚያን የአገር ከተሞች ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አሰበው፥ ሎጥ ተቀምጦበት የነበረውንም ከተማ ባጠፋ ጊዜ ከዚያ ጥፋት መካከል ሎጥን አወጣው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ሎጥ ይኖርባቸው የነበሩትን፥ በሸለቆ የሚገኙትን ከተሞች፥ እግዚአብሔር ባጠፋ ጊዜ አብርሃምን አስታወሰ፤ ስለዚህም ሎጥን ከጥፋት ወደሚድንበት ቦታ መራው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እነ​ዚ​ያን ከተ​ሞ​ችና ሎጥ የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውን አው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋን ሁሉ ባጠፋ ጊዜ አብ​ር​ሃ​ምን ዐሰ​በው፤ ሎጥ​ንም ከጥ​ፋት መካ​ከል አወ​ጣው።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 19:29
21 交叉引用  

የታራም ትውልድ እነሆ ይህ ነው። ታራም አብራምንና ናኮርን ሐራንንም ወለደ፤ ሐራንም ሎጥን ወለደ።


ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ ስምህንም አከብረዋለሁ፤ ለበረከትም ሁን፤


እግዚአብሔር ራሔልን አሰበ፥ እግዚአብሔርም ተለመናት፥ ማኅፀንዋንም ከፈተላት፤


እግዚአብሔርም ኖኅን፤ በመርከብም ከእርሱ ጋር የነበረውን አራዋቱን ሁሉ፤ እንስሳውንም ሁሉ አሰበ።


አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ አስበኝ፥ ለአምላኬም ቤት ያደረግሁትን ወረታዬን አታጥፋ።


ሌዋውያኑንም ራሳቸውን እንዲያነጹ፥ መጥተውም በሮቹን እንዲጠብቁ፥ የሰንበትንም ቀን እንዲቀድሱ ነገርኋቸው። አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ደግሞ አስበኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ራራልኝ።


እንደ አንተ ያለውን ሰው ክፋትህ ይጐዳዋል፥ ለሰውም ልጅ ጽድቅህ ይጠቅመዋል።


እነዚህ ሦስት ሰዎች ቢኖሩባት፥ እኔ ሕያው ነኝና እነርሱ ብቻቸውን ይድናሉ እንጂ ወንዶችንና ሴቶች ልጆቻቸውን አያድኑም፥ ምድሪቱም ባድማ ትሆናለች፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


ኤፍሬም ሆይ፥ እንዴት እጥልሃለሁ? እስራኤል ሆይ፥ እንዴትስ አሳልፌ እሰጥሃለሁ? እንዴትስ እንደ አዳማ እጥልሃለሁ? እንዴትስ እንደ ሲባዩ አደርግሃለሁ? ልቤ በውስጤ ተናውጣለች፥ ምሕረቴም ተነሣሥታለች።


ነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አዳናችሁ።


ባሪያዎችህን አብርሃምንና ይስሐቅን ያዕቆብንም አስብ፤ የዚህን ሕዝብ ደንዳንነት ክፋቱንም ኃጢአቱንም አትመልከት፤


ምድራቸውን ትወርሳት ዘንድ የምትገባው ስለ ጽድቅህና ስለ ልብህ ቅንነት አይደለም፤ ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ከፊትህ በሚያጠፋቸው በእነዚያ አሕዛብ ኃጢአት ምክንያትና ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ቃል ይፈጽም ዘንድ ነው።


ጻድቅ ሎጥም በመካከላቸው ሲኖር እያየና እየሰማ ዕለት ዕለት በዓመፀኛ ሥራቸው ጻድቅ ነፍሱን አስጨንቆ ነበርና በዓመፀኞች ሴሰኛ ኑሮ የተገፋውን ያን ጻድቅ ካዳነ፥


跟着我们:

广告


广告